የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድህን አባልነት በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ሽፋኑን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

    የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድህን በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ሽፋኑ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ የኢትዮጲያ ጤና መድን አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉቀን አርጋውና የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በጋራ በመሆን በዛሬው እለት ለጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል።
    የኢትዮጲያ ጤና መድን አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉቀን አርጋው በጋዜጣዊ መግለጫቸው እንደ ሀገር ከአሁን በፊት በነበረው አሰራር ሰዋች ከኪሳቸው ነበር ገንዘብ አውጥተው የሚታከሙት የጤና ወጪ ያልተጠበቀ በመሆኑ ለድህነት ይጋብዛል ይህም በመሆኑ ማህበረሰቡ የህክምና እና ከህክምና ጋር ተያይዘው በሀገር ውስጥ የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶች ለአንድ አመት የሚቆይ የአባልነት ምዝገባ በማድረግ አገልግሉቱን ያገኛሉ አገልግሎቱን ለማግኘት የጤና መድህን አባል መሆን ይኖርባቸዋል ብለዋል ፡፡
    ዶክተር ሙሉቀን በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የጤና መድህን አባልነት ሽፋን ካገኙት 834 ወረዳች ወደ ተሻለ ቁጥር ለማሳደግ በዚህም በበጀት ዓመት እናሳካለን ብለን በዕቅድ የያዘውን ለማሳካት እንቅስቃሴ መጀመራቸውን አክለው ገልፀዋል፡፡
    ዜጎች ለህክምና ከኪስ የሚያወጡት አላስፈላጊ የወጪ ጫና መቀነስ ያስፈልጋል ሲሉ የገለፀት ዶክተር ሙሉቀን በሀገራችን ከ40 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል።
    የጤና መድን ዘላቂነትን ለማረጋገጥ የአባልነት ምጣኔን በመጨመር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የተገኘውን መልካም አፈፃፀም በማስቀጠል ባለፈው አመት ከነበረው 8.7 ሚሊዮን የአባወራ ብዛት በዚህ አመት ወደ ለ9.4 ሚሊዮን ለማድረስ እየሰሩ እንደሚገኙም ዶ/ር ሙሉቀን ገልፀዋል ፡፡
    የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በበኩሏቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን በድሬዳዋ 2013 ዓ.ም ጀምሮ መጀመሩን በመጥቀስ ይህን መልካም ጅምሮ ለማስቀጠል በ2014 ዓ/ም እየተካሄደ ባለው ምዝገባ አስካሁን ባለው መረጃ በከተማ2% በገጠር 3% መመዝገብ መቻሉን በመጥቀስ የአባላት ቁጥርን ለመጨመር የቅስቀሳ ስራዋችን እየተሰሩ እንዳሉ ገልፀዋል።
    ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን ፕሮግራም ትግበራ በገጠር ከጤና ኬላ አንስቶ በከተማ ለሚገኙ አባላቶቹ የህክምና አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ በመጠቆም አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የጤና መድን አባላት ለብቻ የአንድ መስኳት አገልግሎት እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑን የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም ገልፀዋል።
    ዘላቂነቱንም ለማረጋገጥ የአባልነት ምጣኔ በመጨመር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የተገኘውን መልካም አፈፃፀም ለማስቀጠል ስራዋች እየተገመገሙ እንደሆነም ወ/ሮ ለምለም ገልፀዋል።