በ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ 6 ወራት የተከናወኑ ስራዎች ግምገማ መድረክ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ስራዎች ወቅታቸውን ጠብቀው መገምገማቸው ለቀጣይ መሰራት የሚገባቸውና ያልተከናወኑ ስራዎች ጉድለቶች እንዲሟሉ ለማድረግና የተሻለ አፈጻጸም ያለውን ለመለየትና ለማበረታታት እንዲሁም ክፍተት ያለበትን ለመደገፍ ያስችለናል ብለዋል።
በግምገማው መድረክ 9ኙ የከተማ ቀበሌዎችና 4ቱ የገጠር ክላስተሮች እንዲሁ 3ቱ የመሰረታዊ ፓርቲ ዘርፎች የተሳተፉ ሲሆን ግምገማው ለሶስት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።


