የድሬደዋ አስተዳደር የ2014 በጀት አመት የ100 ቀናት ሪፖርት ግምገማ እየተካሄደ ነው።

    በትላንትና እለት የተጀመረው የ100 ቀናት የስራ አስፈጻሚ ተቋማት ግምገማ ዛሬ ጠዋት የተጠናቀቀ ሲሆን የከተማ ቀበሌዎች እና የገጠር ክላስተሮች የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ከሰአት በኃላ ጀምሮ እስከ ነገ ድረስ የሚገመገም ይሆናል ፡፡
    በሪፖርት ግምገማ መድረኩ ሁሉም ፈፃሚ ተቋማት የመቶ ቀናት የመደበኛ እና የፕሮጀክት የእቅድ አፈፃፀም ሪፓርት አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
    የሪፖርት ግምገማ መድረኩን የመሩት የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጆሀር በሰጡት ግብረ መልስ የተቋማት ስራ አፈፃፀም በርካታ አመርቂ ውጤታቶች የተመዘገበበት መሆኑን አመላክተዋል ነገር ግን የታዩ ክፍቶችን በቀጣይም በላቀ ተነሳሽነት በመስራት ለማህበረሰቡ በገባነው ቃል መሰረት ሰርተን የድሬዳዋን እድገት ማረጋገጥ አለብን በማለት የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
    ከንቲባ ከድር ከዚህም ጋር አያይዘው በማህበረሰቡ ለሚነሱ ጥያቄዋች አመራሩ ምላሽ በመስጠት ለሚመራው ህዝብ አገልጋይ መሆን አለበት በማለት በበጀት አመቱ የተያዘውን እቅድ በላቀ አፈፃፀም በማከናወን የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ወደ ብልፅግና የሚደረገውን ጉዞ እውን ማድረግ አለብን ብለዋል።
    ከዛሬ ከሰአት በኃላ ጀምሮ የከተማ ቀበሌዎች እና የገጠር ክላስተሮች የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ እስከ ነገ ድረስ የሚገመገሙ ይሆናል ፡፡