ጥር 7/2014 ዓ.ም 17ኛው ሳምንት የድሬዳዋ ከተማ አቀፍ የጽዳት ዘመቻ፤ በከንቲባ ከድር ጆሀር መሪነት፤ በአስተዳደሩ የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች አማካኝነት ዛሬ ተከናውኗል።

    በዘመቻው በአስተዳደሩ የሚገኘው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች አመታዊ የጥምቀት በዓል ማክበሪያ ስፍራና አካባቢው የተፀዳ ሲሆን፤የፅእዳት ዘመቻውን የመሩት የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጆሀር ባስተላለፉት መልዕክትም እንደተናገሩት የፅዳት ዘመቻውን ስንጀምር ጁንታውንና የሱ ተላላኪ የሆኑትን ከቆሻሻው ጋር አብረን እናፅዳ በማለት የጀመርነው በመሆኑ የቀሩትንም አብረን እያፀዳን እንቀጥላለን ብለዋል።
    ከንቲባ ከድር ከዚህም ጋር አያይዘው በአሉን ለራሳቸው አጀንዳ ማስፈፀሚያ የሚያደርጉ ስላሉ እኛ በተባበረ ክንዳችንን አጠናክረን ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የእምነቱ ተከታዮች ወንድሞቻችን በዓሉን ያለምንም ስጋት እንዲያከብሩ የድርሻችንን መወጣት ይኖርብናል ሲሉ አሳስበዋል።
    በአስተዳዶሩ ያሉ ቀበሌዋች በአሉን ለማክበር ወደ አደባባይ የወጣውን የእምነቱ ተከታዮች የተለመደውን መስተንግዶ በማድረግ በአሉ በተሳካ መልኩ እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን እንዲወጡ ከንቲባ ከድር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።