”’ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል አደረሳችሁ ”’ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር

    በዓሉ አብሮነታችንን በማጠናከር መልካም እሴቶቻችንን የምናጎላበት ሊሆን እንደሚገባ አቶ ከድር ጁሃር ጥሪ አቅርበዋል።በተለይም ባለፉት አመታት የተለያዩ ሃይማኖታዊ በዓላትን በማስታከክ በህዝቦች መሃል ግጭት እንዲፈጠር በማድረግ የህዝቡን የቆየና የዳበረ የመከባበር፣የመቻቻል ብሎም የወንድማማችነት መንፈስን እንዲላላ ከፍ ሲልም ግጭትና ሁከት እንዲፈጠር በተለያዩ አካላት ጥረት ሲደረግ መስተዋሉን አውስተዋል።
    በመሆኑም የድሬደዋ ነዋሪ በሃይማኖት ሽፋን ጥፋት ለማድረስ ሙከራ የሚያደርጉ አካላትን እኩይ ሴራ በመገንዘብ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀነናጀት በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ማሰቻል ይገባል ሲሉ አቶ ከድር ጁሀር ጥሪ አቅርበዋል።
    ከበአሉ ጋር በተያያዘ ከክርስትና እምነት ተከታዮች ውጪ ያሉ የሌሎች እምነት ተከታዮች የአስተዳደሩ ነዋሪዎች በአሉን ከእምነቱ ተከታዮች ጋር በወንድማማችነት መንፈስ የማክበር የቆየና የዳበረ ልምዳችን ማስቀጠል ይገባልም ብለዋል ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር።