የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው ደንብ ላይ ለአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተሰጠው ስልጠና
የአስተዳደሩ ከንቲባ የተከበሩ ከድር ጁሀር ባደረጉት ንግግር እንደተናገሩት የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ባለንበት ወቅት በየደረጃው ያለው አመራር ተገቢውን የስነ ልቦና ዝግጅት በማድረግ በእውቀትና በአገልጋይነት መንፈስ የመሪነት ሚናቸውን በግንባር ቀደምትነት መወጣት ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ከንቲባ ከድር ከዚህም ጋር አያይዘው የአስተዳደሩ ነዋሪዋች የአዋጁን ጠቀሜታና አስፈላጊነት በመረዳት የአዋጁ አፈፃፀም ውጤታማ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የአስተዳደሩ ከንታባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን በበኩላቸው ይህ ስልጠና ለአመራሩ መሰጠቱ ከዚህ ቀደም በካሳ ክፍያ ዙሪያ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ በተሻሻለው አዋጅ ለማስፈፀምና አመራሮች ተናበን በመስራት በልማት ተነሺዋች ያለውን ቅሪታ በደንቡ መሰረት ለመፍታት ያስችለናል ብለዋል።
የጽ/ ቤቱ ኃላፊ አቶ ገበየሁ ከዚህም ጋር አያይዘው በልማት ተነሺዋችም ከዚህ በፊት የነበረው ችግር አዋጁ በመቅረፉ ደስ እያላቸው ለልማቱ መሳካት እገዛ በማድረግ የድርሻቸውን እንዲወጡ የሚያስችል ነው በማለት።ስልጠናው እስከታች ድረስ በመውረድ በማሰልጠን የተፈለገው ውጤት እንዲመጣ እንደሚሰራ ገልፀዋል።
በመጨረሻም በስልጠና ተሳታፊዋችም በቀረበው የአዋጁ ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።


