የድሬ ዳዋ አስተዳደር ምክር ቤትን ካተማ ልማት፣ኮንስትራክሽንና ማዘጋጃቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመስክ ምልከታ ዛሬ በ4ኛ ቀኑ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ተመልክቷል ።

    የድሬ ዳዋ አስተዳደር ምክር ቤትን ካተማ ልማት፣ኮንስትራክሽንና ማዘጋጃቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመስክ ምልከታ ዛሬ በ4ኛ ቀኑ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ተመልክቷል ።
    ኮሚቴው በዛሬው ዕለት በከተማው የተሰሩትና እየተሰሩ ያሉት በርካታ የልማት ፕሮጀክቶችን ሲጎበኝ የዋለ ሲሆን የኮንትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ ለቢሯቸው እያስገነባ ያለውን የ G+4 ና G+5 ህንፃ ግንባታ ያለበትን ደረጃ ከባለፈው 3 ወር በፊቱ መልከታ ጋር በማነፃፀር ገምግሟል።
    ከ3 ወር በፊት 92% ደረጃ ላይ የደረሰ የ G+4ቱ ህንፃ ግንባታ ዛሬ ላይ 96% ለይ መድረሱንና በ 3 ወር ውስጥ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ተገልጿል። በተጨማሪም በህብረተሰብ ተሳትፎና ልማት ኤጀንሲ እየተገነቡ ያሉትን የልማት ፕሮጀክቶች በተለይም 04 ቀበሌ የተገነባውን የቀበሌውን የገቢ ማሰባሰቢያ ወፍጮ ቤት ፣ በ05 ቀበሌ እየተገነቡ ያሉትን 2 የከፍታ መንገዶችና በ 05 ና 06 ቀበሌ አየተሰሩ ያሉትን የቀበሌ ቤቶች የጋራ መፀዳጃ ቤቶችና በ03 ቀበሌ በአሸዋ ዳር እየተገነባ የለውን የከብቶች መሸጫ ሼድ ግንባታ ፕሮጀክት የግንባታ ሁኔታና ያለበትን ደረጃ ተመልክቷል።
    ቋሚ ኮሚቴው በ03 ቀበሌ የተጀመረው የከብቶች መሸጫ ሼድ ግንባታ ሂደት መቋረጡንም የተመለከተ ሲሆን ኮሚቴዉ በነገዉ ዕለት መረሃ ግብሩ በምልከታዉ የታዩ ዉስንነቶችና በተሻሻሉ አፈጻጸሞች ዙሪያ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር የሚወያይ ይሆናል።