ላለፉት አራት ቀናት በድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት እንዲሁም በሳቢያን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሲሰጥ የቆየዉ የብልጽግና ፓርቲ አባላት የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች አቅም ግንባታ ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል ፡፡
“አዲስ ፖለቲካዊ እይታ፤ አዲስ ሀገራዊ እምርታ” በሚል መሪ ቃል ለተከታታይ 4 ቀናት የብልጽግና ፓርቲ አባላት የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች አቅም ግንባት ስልጠና ከሀሙስ ቀን ግንቦት 25 / 2014 ጀምሮ በሁለት የስልጠና ማዕከላት በ4 የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲሰጥ ቆይቷል ።
በተካሄዱት ተከታታይ የ4 ቀናት ስልጠና በ አራት የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የተዘጋጁ ሰነዶች በካቢኔ ደረጃ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች የቀረበ ሲሆን በቀረበዉ ሰነድ ላይ ሰልጣኞች በሰፊዉ ተወያይተዉበት ግልጽ ያልሆነላቸዉ ሃሳቦች ላይ የሚያነሱት ጥያቄ ከበቂ ማብራሪያ ጋር ምላሽ የሚሰጥበት
የ ስልጠና ሂደት የነበረ ሲሆን በዛሬዉ የማጠቃለያ ቀን ርዕሰ ጉዳይ የሆነዉ የመደመር ጽንሰ ሀሳብ ተቋማዊ ግንባታ ላይ ያተኮረ ሰነድ በአሰተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ሃለፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ ቀርቦ በተሳታፊዎች በጥልቀት ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ከዉይይቱ ቡኃላ ለተነሱ ጥያቄዎችም ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥቷል ።
የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በሳቢያን 2ተኛደረጃ ት/ቤት የሰልጠና ማዕከል በመገኘት ለሰልጣኞች ባሰተላለፉት የማጠቃለያ ሃሳብ አመራሩና አባሉ ከአሰተሳሰብ ጋር የተዋሀደ እንዲሆን ዕይታን ለመቀየር የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት አደረጃጀቶችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልጸዉ በየደረጃዉ ያለዉ አመራርና አባል የብልጽግና አስተሳሰብ ባለቤትና ግንባር ቀደም ሆኖ ሊመራ ይገባል ብለዋል፡፡
ሃላፊው አክለውም ህዝቡ የሚፈልጋቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በአፋጣኝ በቁርጠኝነት መመለስ እንደሚገባ እንሁዲም አመራሩን እና አባሉን በማጥራትና በማብቃት ጠንካራ መንግስትና ፓርቲን በመገንባት እና ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ጉድለቶችን በማስተካከል ጠንክረን በቁርጠኝነት ከሰራን ሁሉን አቀፍ የብልጽግና ከፍታ ላይ መዉጣት እንችላለን ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ያነጋገርናቸው የስልጠና መድረኩ ተሳታፊዎችም ስልጠናው የፓርቲውን ራዕይ ከየት ተነስተን የት እንደምንደርስ በግልጽ የተቀመጠ እና አቅምን የሚገነባ ስልጠና መሆኑ እና ሁሉም አባላት የሀሳብ ብልጽግና በማምጣት ስልጠናውን ወደ ውጤት ለመቀየር መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡
በሳቢያን 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት በተዘጋጀዉ ስልጠና ላይ ከ1300 በላይ የሆኑ ሰልጣኞች ተሳትፈዋል።


