በዋሂል ክላስተር የለገኦዳ ጉኑፈታ ገጠር ቀበሌ ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ ቀበሌ በመሆን የማረጋገጫ እውቅና ተሰጠው፡፡

    በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የሃይጂንና አካባቢ ጤና አጠባብቅ ኬዝ ቲም እና በዋሂል ክላስተር እንዲሁም በለገኦዳ ጉኑፈታ ገጠር ቀበሌ አመራሮችና በህብረተሰቡ ከፍተኛ ተሳትፎ በተሠሩ ሥራዎች የለገኦዳ ጉኑፈታ ገጠር ቀበሌ ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ መሆኑ ታውጇል፡፡
    በለገኦዳ ጉኑፈታ ገጠር ቀበሌ በተካሄደው የዕውቅና አሰጣጥ መረሃ ግብር ላይ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚንስትር ደኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማና ሌሎች ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከዲር ጁሃርና የብልፅግና ፅ/ቤት አመራች እንዲሁም ሌሎች የአስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ባለድረሻ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
    ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ ቀበሌ ባለቤት የሆናችሁ የለገኦዳ ጉኑፈታ ገጠር ቀበሌ ነዋሪዎችና አመራሮች እንኳን ደስ ያላችሁ ያሉት ሚንስቴር ዲኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ቀበሌያችሁን ሜዳ ላይ ከመፀዳት ነፃ ለማውጣት ያደረጋችሁት ርብርብ የህፃናትንና የእናቶችን እዲሁም የሁላችሁንም ጤና ለመጠበቅ ፋይዳው ከፍ ያለ በመሆኑ ለሠራችሁት ሥራ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ ብለዋል፡፡ ዶ/ር ደረጀ አያይዘውም ቀበሌን ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ ማውጣት አንዴና በሆነ አጋጣሚ ብቻ ተሠርቶ የሚያበቃ ሳይሆን ቀጣይነት ሊኖረውና ሁሌም ሊሠራ የሚገባው በመሆኑ ዛሬ ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ የወጣውን ቀበሌያችሁን የተሰጠውን እውቅና አስጠብቃችሁ ጤናማ ማህበረሰብ ይኖራችሁ ዘንድ ተግታችሁ እንድትሠሩ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ ብለዋል፡፡
    የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቱባ አቶ ከድር ጁሃር በበኩላቸው የለገኦዳ ጉኑንፈታ ገጠር ቀበሌ ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ በመሆናችሁ ለቀበሌው ማህበረሰቦች የተሰማኝን ደስታ ልገልፅ እወዳለሁ ያሉ ሲሆን ለዚህ ውጤት ከፍተኛ ጥረት ስታደርጉ የነበራችሁ የክላስተር፣ የቀበሌውና እንዲሁም የድሬዳዋ ጤና ቢሮ አመራችና ሠራተኞች አንዲሁም ለባለድርሻ አካላት ምስጋናዬን እያቀረብኩ የግልና የአካባቢውን ንፅህና የሚጠብቅ ማህረሰብ እንዲኖረን ሁሌም ተግተን ልንሠራ ይገባል ብለዋል፡፡
    የጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በገጠር ቀበሌው ሁሉም ቤተሰብ የመፃዳጃ ቤት ባለቤት በመሆን ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ ቀበሌ ሊሆን በመቻሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ቀበሌውን ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ ለማድረግ ርብርብ ሲያደርጉ ለነበሩ ሁሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ ብለዋል፡፡
    ለዚህ ሥራ ስኬት ይረዳ ዘንድ ቢሮው ለተለያዩ የምህበረሰብ ክፍሎች፤ የክላስተርና የቀበሌው አመራሮች ስልጠናዎችን ከመስጠቱም ባሻገር ወጣቶችን በማደራጀት የሳኒቴሽን ማርኬቲንግ እውን ለማድረግ ሞያዊ ስልጠናዎችን በመስጠት ለመፀዳጃ ቤት ግብአት የሚሆኑ ቁሶችን እንዲያመርቱ የተቻለ በመሆኑ በቀጣይም እነዚህ ወጣቶች በቀበሌያችሁ ውስጥ የሚያመርቷቸውን ግብዓቶች በመግዛት ልታበረቷቷቸውና ካላስፈላጊ ወጪ እራሳችሁን ልታወጡ ገይባል ብለዋል፡፡
    ሜዳ ላይ ከመጸዳዳት ነፃ ለወጣው የለገኦዳ ጉኑፈታ ገጠር ቀበሌ የዋንጫ፣ የእውቅና ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትና የቴለቪዢን ሽልማት ተበርክቷል፡ሲል መረጃዉን ያደረሰን