የናፍቆት ድሬዳዋ ሳምንትን በታላቅ ድምቀት ለማክበር በአስተዳደር ደረጃ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው ።

    በተለያዩ የአለማችን ሀገራት እንዲሁም በሀገራችን ኢትዮጲያ ላይ ባሉ ከተሞች ላይ የሚገኙ የድሬዳዋ ተወላጆችና ወዳጆች የፍቅር የአንድነትና የመቻቻል ከተማ በሆነችው የድሬዳዋ ከተማ ላይ በሚካሄደው የናፍቆት ድሬዳዋ ሳምንት ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ይኸውም ፕሮግራም ከፊታችን ሀምሌ 11 እስከ ሀምሌ 16 2014 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ መርሀ-ግብሮች በታላቅ ድምቀትም ይከበራል ።
    የናፍቆት ድሬዳዋ ሳምንት በስኬት ይከናወን ዘንድ በአስተዳደር ደረጃ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተካሄዱ የሚገኙ ሲሆን በአሉ ላይም ለመታደም ከተለያዩ ሀገራት ወደ ትውልድ ከተማቸው እንግዶች በመምጣት ላይ ይገኛሉ ።
    ለዚሁ ፕሮግራም ሲባልም በአስተዳደር ደረጃ የተዋቀረው ኮሚቴ በየሳምንቱ ማክሰኞ እና አርብ መደበኛ የኮሚቴ ስብሰባ የሚያደርግ ሲሆን ኮሚቴው በዛሬው እለት ባደረገው ስብሰባም የፋይናንስ ስርዓቱ በማዕከል ብሎክ አካውንት ተከፍቶ እንዲተዳደርና የንኡስ ኮሚቴ ተግባራት በታቀደላቸው ቀናት እንዲከናወኑ ከስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የንግድ ቀንና የባቡር ቀን በቅንጅት እንዲከበር ነው በስብሰባው ላይ የተወሰነው ።