ሰኔ 07 ቀን 2014 የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ::

    ኢትዮጵያን በከፍተኛ ሁኔታ እየተፈታተነ የሚገኘውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር የተጀመሩት ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡
    ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያዌዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡
    በማብራሪያቸው ባለፉት አራት አመታት በበርካታ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ችግሮች አገሪቱ መፈተኗን ጠቅሰዋል።
    ያጋጠሙ ችግሮች የፈጠሯቸውን እድሎች በመጠቀም ኢኮኖሚው ላይ ጫና እንዳይፈጠር ሲሰራ መቆየቱን ገልጸው፤ የዋጋ ንረት በከፍተኛ ሁኔታ ኢኮኖሚው ላይ ጫና እየፈጠረ ነው ብለዋል፡፡
    የዋጋ ንረቱ በተለይ በዝቅተኛው የህብረተሰብ ክፍል ላይ ጫና እንዳይፈጥር የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
    ከጥረቶቹ መካከልም በመብራት፣ በውሃ፣ በነዳጅ እንዲሁም በማዳበሪያ ምርቶች እና አገልግሎቶች ላይ ድጎማ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
    ለአብነትም በአዲስ አበባ ብቻ ከ628 ሺህ በላይ የተማሪዎች ምገባ መደረጉን፣ በሁለት የዳቦ ፋብሪካዎች አማካኝነት በቀን ከ 3 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ዳቦ ማምረት መቻሉን ገልጸዋል።
    እንዲሁም ከ80 በላይ የእሁድ ገበያዎችን ወደ ስራ በማስገባት የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ጥረት መደረጉን ተናግረዋል፡፡
    ኢ.ዜ.አ