የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ በመዲናችን በአዲስ አበባ ከተማ በመከናወን ላይ የሚገኙና በሰብዓዊ ልማት ላይ ያተኮሩ የጓሮ ግብርና ሥራዎችንና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማኅበረሰብ ክፍሎች ለመመገብ የሚያስችሉ የምገባ ማዕከላትን ተዘዋዉረዉ ተጎብኝቷል ። እንደዚህ ያሉት ሥራዎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆናቸዉን የገለጹት ክቡር ጠቅላይ ሚኒሰቴር ዶ/ር አብይ አህመድ እንድህ አይነት ሰብአዊ ልማት ላይ ያተኮሩ የጓሮ ግብርና ስራዎች በሁሉም አካባቢዎች በስፋት ሊከናወኑ ያስፈልጋል ብለዋል


