ሲሚንቶን በጅንአድ በኩል መቅረብ መጀመሩ ተገለፀ። የአንድ ኩንታል ሲሚንቶ ዋጋም 730 ብር መሆኑ ተጠቁሟል።

    የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ በአስተዳደሩ ያለውን የሲሚንቶ ዋጋ ንረት ለመቆጣጠር፤ ከሰኔ 18 ጀምሮ የሲሚንቶ ምርትን በጅንአድ ማከፋፈል መጀመሩን አስታውቋል።
    ማንኛውም የአስተዳደሩ ነዋሪ የታደሰ መታወቂያ እና የግንባታ ፈቃድ በመያዝ ከጅንአድ ሲሚንቶ መግዛት እንደሚችል ተገልጿል።
    የአንድ ኩንታል የሲሚንቶ ዋጋ መንግስት ባስቀመጠው ዋጋ መሰረት 730 ብር ብቻ መሆኑም ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።