የድሬዳዋ አስተዳደር የ2014 በጀት አመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ ዛሬ ጀምሯል የግምገማ መድረኩ ነገም ይቀጥላል ።

    በዛሬው እለትም የሴክተር መስሪያ ቤት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ 6 ተቋማት ማለትም ትምህርት ቢሮ ፣ግብርና ውሃ ማዕድን ኢነርጂ ቢሮ፣የስራ ክህሎት ና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ፣ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ እና የቤቶች ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የ2014 ዓ.ም በጀት አመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
    የተቋማቱ የትኩረት መስኮች በተለይም በአስተዳደሩ ምክር ቤት፣ በክብር ከንቲባው የተሰጡትን አስተያየት እንዲሁም ህብረተሰቡ እና ባለድርሻ አካላት ያነሷቸውን ጥያቄዎች ታሳቢ በማድረግ እና ከተቋሙ ቁልፍ ተግባራት ጋር በማዋሀድ ታቅደው የተፈጸሙ መሆኑ ነው በሪፖርቱ የተገለጸው፡፡
    የንግድ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ፡- አዲስ እና መካከለኛ ማኒፋክቸሪንግን ማበራከት ፣ በስራ እድል ፈጠራ ፣የኢንዱስትሪ ሽግግር እና የእምቅ ሀብት ክምችት ማሳደግ የሚሉ ቁልፍ ተግባራት ከእቅድ አንጻር ጥሩ አፈጻጸም የነበራቸው መሆኑ በሪፖርቱ ተጠቅሷል ፡፡
    በትምህርት ዘርፍ፡- የትምህርት ተሳትፎንና የልዩ ፍላጎት ትምህርትን ማሳደግ፣፣የትምህርት ጥራትን ማጎልበት፣ የተማሪ ውጤት ማሻሻል ፣የመመሪያ መጽሀፍትን ተደራሽ ማድረግ የተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት እንዲሁም በሳይንስ ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች እና በገጠር የሁለተኛ ደረጃ ትምህረት ቤት በዘንድሮ አመት ሙሉ ለሙሉ የኢንተርኔት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል ጥሩ አፈጻጸም የነበራቸው ሲሆን የብሄራዊ ፈተናዎች አንደኛ ደረጃ የከፍተኛ ትምህረት መግቢያ ላይ መጠነ ማለፍ በአንደኛ ደረጃ ጥሩ ቢሆንም የከፍተኛ ትምህረት ላይ ውስንነቶች መኖሩ እንዲሁም በካፒታል ፕሮጀክት የተያዙ የትምህረት ተደራሽነትን ከማሳደግ አንጸር የትምርት ቤት ግንባታ ፕሮጀክቶች በታለመላቸው ጊዜ ገደብ ያላለቁ መሆናቸው በሪፖርቱ ተብራርተዋል፡፡
    የግብርና ውሃ ማእድን ኢነርጂ ቢሮ ፡- ምርትና ምርታማነትን ማሻሻል የተፈጥሮ ሀብት ስራን ማጎልበት የእንስሳት ሀብት ልማትን ማሻሻል ዘላቂ የውሃ ሀብት ልማት የህብረት ስራ ማህበራትን ማስፋት የመልካም አስተዳደር የባለ ብዙ ዘርፍ አፈጻጸም እና የካፒታል ፕሮጀክት አፈጻጸም ቀርበዋል፡፡
    ምርት ና ምርታማነትን ከማሳደግ አንጻር የማሳ ዝግጅት እንዲሁም ከፍተኛ ትኩረት ተሰቶት የተሰራው የመስኖ ልማት ሰራ ሰፊ ርብርብ የተደረገበት የአትክልት ልማት ፓኬጅ 424 አርሶ አደሮች በቲማቲም ሽንኩርት ቃሪያ እና በሰብል ምርቶች በንቅናቄ የተሳተፉበት፣በከተማ ግብርና ዘር የማህረሰብ ንቅናቄ በኤክስቴንሽን ሙያዊ ድጋፍ መስጠት ለ1750 ታቅዶ ለ1725 ተጠቃሚዎች አገልገሎት እንዲያገኙ ተችሏል በዚህም 98% የእቅዱን ማሳካት እንደተቻለ የአፈር እና ውሃ ጥበቃ ስራዎች ማሳደግ የእቅዱን 62% ማሳካት መቻሉን የጥምር እርሻ ደን ልማት ማስፋት የእቅዱን 100% መፈጸሙን ፣የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት በገጠር ለ13.700 የማህበረሰብ ክፍሎች፣የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረጉን ፣ ጥገና የሚያስፈልጋቸው 30 የውሃ ቱቦዎች ሙሉ ለሙሉ ጥገና መደረጉን እንዲሁም የካፒታል ፕሮጀክት የግድብ ስራ መስኖ ልማት የፕሮጀክት አፈጻጸም በጥሩ የታዩ መሆናቸው የተመላከተ ሲሆን በተግዳሮት የተነሱት በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ የዝናብ አጥረት በመኖሩ የተዘሩ ዘሮች ውጤታማ አለመሆናቸውም ተገልጿል፡፡
    የስራ ክህሎት እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ፡- ትምህርት እና ስልጠና ፍትሀዊነት እና ተደራሽነትን ማሳደግ የሙያ ብቃት ምዘና የክትትል እና ድጋፍ ስራዎች አጠቃላይ የተቋሙ አበይት ተግባራት አፈጻጸም ከእቅድ አንጻር የተሻለ መሆኑ ተገልጿል፡፡
    ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ፡- ገቢን ከማሳደግ አንጻር መዘጋጃ ቤታዊ ገቢዎች እንዲሁም የታክስ ገቢዎች እቅድ አፈጻጸም 91% መፈጸሙ፣ ስራ ማስኬጃ እና ደሞዝ የእቅዱን 95% መፈጸም መቻሉ የሀብት ምንጭ እና አጠቃቀምን ማደግ ፣ወጪ ቆጣቢ ስልቶችን ማሳደግ የካፒታል ፕሮጀክት በተሻለ አፈጻጸም የታዩ መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
    ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ የህንጻ ቁጥጥርና ክትትል፣በህብረተሰብ ተሳትፎ ንቅናቄ የተሰሩ 235 ታቅዶ 215 ክንውን መሆኑን የነባር የካፒታል ፕሮጀክት አፈጻጸም 50% መሆኑ ተገልጿል፡፡በቀረቡት ሪፖርት ዙሪያ ተሳታፊዎች ሀሳብ አስተያየት ጥያቄዎች በስፋት ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
    በመጨረሻም ክብር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በስራዎች አፈጻጸም ላይ አስተያየት እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችን የሰጡ ሲሆን የትምህርት ፍኖተ ካርታ ላይ ያሉትን እያንዳንዱ ተግባራት እንዲፈጸሙ፣ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት ፣ የተማሪ ውጤት ማሻሻል የገጠር ትምህርት የመማር ማስተማር ሂደት ፣የግል ትምርት ቤት የዋጋ ጭማሪ እንዲሁም የመጠነ ማቋረጥ የክትትል እና ቁጥጥር ስራዎች መጠናከር እንዳለባቸው ክብር ከንቲባው አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡
    በንግድ እና ኢንዱስትሪ የሲሚንቶ የግብይት ስርአቱ ጋር በተያያዘ ከግብርና ውሃ ማዕድን ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን የግብይት ሰንሰለት ውስጥ የህብረት ስራ ማህበራት ለሸማቾች የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ኢንቨስትመንትን ከማሳደግ አንጻር ስራዎች መጠናከር እንዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡
    በግብርና ምርት እና ምርታማነትን ከማሳደግ ጋር በተያያዘ ፣የእንስሳት ሀብት ልማት፣የከተማ ግብርና ላይ የንቅናቄ ስራዎች፣ማህበራትን አቅም እንዲሁም የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት በቀጣይ አመት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ከንቲባው አስረድተዋል፡፡
    የስራ ክህሎት እና ቴክኖሎጂ ልማት በአጭር ጊዜተቋሙ ተቋቁሞ ወደ ግብ ተኮር የስራ እቅድ በመግባት ጥሩ አፈጸጸም የታየበት መሆኑ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ ብድር ማስመለስ ላይ የኮሌጅ ብቃት ላይ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት አስረድተዋል፡፡ ገንዘብ ና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የፕሮጀክት አፈጻጸም ላይ እንዲሁም ግዢ በእቅድ መመራት እንዳለበትም አስገንዝበዋል፡፡
    ኮንስትራክሽን ላይ የጨረታ ዋጋ የተጋነነ መሆን ከኮንዶሚኒየም የይዞታ እና የተቋሙ የሪፎርም ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ አሳስበዋል፡፡
    በከሰዕቱም ውሎ ከተማ ስራ አስኪያጅ ቢሮ፣ መሬት ልማት፣ ጤና ቢሮ፣ሴቶች ህፃናት ጉዳይ ቢሮ እቅዶቻቸውን አቅርበዋል በነገው እለትም ሌሎች ተቋማት የሚቀጥሉ ይሆናሉ