የ2014 በጀት አመት የ4ኛው ሩብ አመት የማዘጋጃ ቤታዊ ፣ የሴክተር መ/ቤቶች ፤የከተማ ቀበሌዎችና የገጠር ክላስተሮች የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ መድረክ ከሰኔ 27-28 /2014 ዓ.ም የሚቆይ ሲሄን በዛሬ ጠዋት የግምገማ መድረክ የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ፤የትምህርት ቢሮ ፣የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ፣የኮንሰትራክሽንና ቤቶች ልማትቢሮ፣ ግብርና ውሀ ማአድንና ኢነርጂ ቢሮና የስራ ክህሎት እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እንዲሁም ቤቶች ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የ4 ሩብ አመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው በተሳታፊዎች አስተያየት ተሰቶባቸዋል ፡፡
የግምገማውን መድረክ የመሩት የአስተዳደሩ ምክትል ከኒትባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ በቀረቡት ሪፖርት ላይ ዝቅተኛ አፈፃፀም ያሏቸው ተቋማት በቀጣይ ትኩረት ተሰቶባቸው መሰራት እንዳለባቸው አቅጣጫ አስቀምጠዋል ፡፡


