የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የ2014 አመታዊ የፓርቲ ስራዎች እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የግምገማ መድረክ መካሄድ ተጀምሯል።

    የ2014 በጀት አመት የ9ኙ ከተማ ቀበሌዎችና 4ቱ የገጠር ክላስተሮች ፓርቲ ጽ/ቤት እንዲሁም የ3ቱ ዘርፎች የመሰረታዊ ፓርቲ የፓርቲ ስራዎች የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ መድረክ ከሰኔ 27-29 /2014 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡
    በዛሬው እለት ከቀበሌ 01 እስከ ቀበሌ 04 የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ መድረክ በከሰዓት መረሃግብር የሚካሄድ ሲሆን ቀሪዎች ቀበሌዎች፣ ገጠር ክላስተሮችና ዘርፎች በቅደም ተከተል የሚያቀርቡ መሆኑ ተገልጿል።
    በመጨረሻ የፓርቲ ስራዎች አመት አፈጻጸም በተጨማሪ በበጀት አመቱ የታቀዱ የ90 ቀናት የስራ አፈጻጸም የሚቀርብ መሆኑን የግምገማ መድረኩን የመሩት የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሻክር አህመድ ተናግረዋል ሲል የቅሪንጫፍ ጽ/ቤቱ ህዝብግንኙነት ክፍል ዘግቧል።