በመንገዳችን ላይ የሚያጋጥሙንን ችግሮች ተቋቁመን ማለፍ ከቻልን፤ መሰናክሎች የዕድገት እና የመሻሻል ዕድሎች ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።
በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ባለፍንባቸው ጊዜያት፤ ጎን ለጎን በጎ ነገሮችንም መፍጠር ችለናል ብለዋል ጠቅላይ ሚስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት አስተያየት።
የተለያዩ መሰናክሎችን በመቋቋም ጭምር በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች የጠንካራ ሥራ ውጤቶች ናቸው ብለዋል ዶ/ር ዐቢይ።
ፕሮጀክቶቹ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተሰነቀው ራዕይ ማሳያ ምልክቶች ናቸው ነው ያሉት።


