የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የ2014 አመታዊ የፓርቲ ስራዎች እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የግምገማ መድረክ ተካሄደ ።

    በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ 9 የከተማ ቀበሌዎችና 4 ቱ የገጠር ክላስተሮች በ 2014 በጀት አመት የ ፓርቲ ፅህፈት ቤት እንዲሁም የ 3ቱ ዘርፎች የመሰረታዊ ፓርቲ በበጀት አመቱ ያቀዷቸውን ስራዎች እንዴት እንደፈፀሙ በዝርዝር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት የሚቀርብበት የግምገማ መድረክ በምክር ቤት አዳራሽ ተካሂዷል ፡፡
    በ 2015 በጀት አመት ከብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት የወረደውን የትኩረት አቅጣጫዎች ለፅህፈት ቤቶች አቅጣጫ በማስቀመጥ በቀጣይ በጀት አመትም በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የሚገመግሙበት መድረክ መሆኑን የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ ደረጄ ፀጋዬ ተናግረው በ 90 ቀን ውስጥ የሚፈፀሙ በተለይም ብልፅግና ፓርቲ ያሉበትና መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አተኩሮ የ 90 ቀን እቅድ እንደተዘጋጀና ይህንንም እቅድ በመገምገም አቅጣጫ የሚቀመጥበት መድረክ እንደሆነም አቶ ደረጄ ፀጋዬ ተናግረዋል ።
    በአስተዳደሩ ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ የተካሄደውን የግምገማ መድረክም የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ምክትል ሀላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሻክር አህመድ አህመድ እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ ደረጄ ፀጋዬ መርተውታል ።