የዝናብ ወቅት መራዘምን ተከትሎ በገጠር ቀበሌዎች ንፁ የመጠጥ ውሀ አቅርቦት፣ የእንስሳት መኖ የሚደረገው ስርጭት ተጠናክሮ መቀጠሉን።በግብርና ውሃ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ የውሃ መስኖ ልማት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ፉአድ መሃመድገልጸዋል።
ችግሩን ለመቋቋም እየተደረገ ባለው ጥረት ቀድሞ በተደረጉ ዳሰሳዊ ጥናቶችን መሰረት በማድረግ በተለይ ከውሃና ከመስኖ ልማት ጋር በተያያዘ ያሉ አማራጮችን በሙሉ አቅም ጥቅም ላይ ለማዋል እየተሰራ እንደሚገኝ ሓላፊው አስረድተዋል።
ድጋፉ አርሶ አርብቶ አደሩ ያለውን ሃብት እንዳያጣ እንዲሁም ችግሩን ለመቋቋም እንደሚረዳ ተናግረዋል።
ከመንግስት ባለፈ በጉዳዩ ላይ የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ከፍተኛ እገዛ እያደረጉ መሆኑን ያስታወቁት አቶ ፉአድ ያጋጠመው ችግር ሳይባባስ ለመግታት ተጨማሪ ድጋፎች እንደሚያስፈልጉ ጠቁመዋል።
አሁን ላይ ለከብቶች እንዲሁም ለሰው የሚሆን የመጠጥ ውሃ ተጨማሪ ቦቴ መኪናዎችን በመከራየት ጭምር ችግሩ ያለባቸው የገጠር ቀበሌዎች እንዲደርስ እየተደረገ እንደሚገኝ ሃላፊው ጠቁመዋል።
ድጋፉ እየተደረገ ባለባቸው ቀበሌዎች ተዘዋውረን ባደረግነው ምልከታ የከብቶች መኖን ጨምሮ ለሰውና የእንስሳት የሚውል የውሃ ስረጭት አየተደረገ መሆኑን እንዲሁም ቶሎ የሚደርሱ ምርጥ ዘሮች መከፋፈሉን ለመረዳት ችለናል።
የድጋፉ ተጠቃሚ ከሆኑት ያነጋገርናቸው አርሶ አርብቶ አደሮች እንደገለፁን መንግስት ለተከሰተው አደጋ ላደረገው አፋጣኝ ምላሽ አመስግነዋል።ይሁን እንጂ ድጋፉ ከደረሰው ችግር አኳያ ሲታይ ሙሉ ለሙሉ በቂ አለመሆኑንና እጥረት እንዳለ አስረድተዋል።


