የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት ፣ ኢኮኖሚ ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የድሬዳዋ አስተዳደርን የስራ ፣ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ2014 በጀት አመት መደበኛ ስራዎችና የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ሪፖርት የቢሮው ሃላፊ የተከበሩ አቶ ሮቤል ጌታቸው በተገኙበት ተገምግሟል፡፡
በቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አይናለም ተዘራ በተሰጠው አቅጣጫም ቢሮው አዲስ እንደመሆኑ መጠን በርካታ ተጨባጭ ስራዎች የተከናወኑ ቢሆንም በአንጻሩ ከበጀት ውስንነት ጋር ተያይዞ መከናወን ሲገባቸው ያልተከናወኑ ስራዎች ለ2015 በጀት አመት የእቅድ አካል ተደርገው እንዲሰራባቸው አቅጣጫ ተሰጥቷል።


