ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየዉ የድሬደዋዳደር የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ ተጠናቀቀ። በግምገማ መድረኩ የተለያዩ አስፈጻሚ አካላት የስራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን አቅርበዋል፡፡

    ሰኔ 27/2014 ዓ.ም የተጀመረው የድሬዳዋ አስተዳደር የ2014 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ መድረክ በትላንትናው ውሎው የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ፣የፍትህ፣ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮና የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የስራ አፈጻጸምን ገምግሟል፡፡
    ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን ተሳታፊዎቹ ላነሷቸው ጥያቄዎችም ሪፖርት ያቀረቡት ተቋማት የስራ ሃላፊዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
    በእለቱ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ባቀረቡ ተቋማት የተለያዩ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን ቤቶች ልማትና ኮንስትክሽን ቢሮ የኮብልስቶን ማህበራት ማጥራት ፤እስከ ሀምሌ 30 ፍትሀዊነት ያለው የመሰረተ ልማት ስራ በ9ኙ ከተማ ቀበሌዎች መኖሩን መፈተሽ እንደሚገባ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡
    የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤትም የከባድ መኪና ላይ ያለው የመፍትሄ አስጣጡ ጊዜያዊ በመሆኑ ቋሚ የሆነ መፍትሄ መሰጠት እንዳለበትና በከተማዋ ያለው የጽዳት ስራም በአመራሩ ብቻ የሚሰራው በቂ ባለመሆኑ የተጠናከረ ስራ ሊኖር እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን የደንብ አስከባሪ መልሶ የማደራጀት ስራ መሰራት አለበት ተብሏል፡፡
    የፍትህ ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ በከተማዋ በተለያዩ ቦታዎች የሀሺሽ ማጨስ ላይ ያሉ ጉዳዮችን ለማጥፋት በደንብ መሰራት እንዳለበታ የተገለጸ ሺኆን አለበት የህገወጥ ሰፈራን የመከላከሉ ስራ ተጠናክሮ መሰራት እነዳለበት እንዲሁም የሮንድ ስራው ተጠናክሮ መሰራት እነዳለበት ተነስቷል፡፡
    ከሚኒሻ ጋር ተያይዞ አላማውን የሳተ ተግባራት እንዳይኖር የመደበኛ የጸጥታ ስራ እንዲሰሩ ሳይሆን የአካባቢያቸውን ሰላም እንዲጠብቁ የማድረጉን ስራ በማጠናከር የሰላም እሴት ግንባታ ስራዎች መጠናከር እንዳለባቸው ተገልጻል፡፡
    የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ቢሮ ጋር ተያይዞም በሪፖርት ግምገማ መድረኩ በተነሳው ሀሳብ ተቋሙ ቀደም ባሉት ወራት በአስተዳደሩ ያሉ ተቋማት ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት እንዲሰጡ ጥሩ እንቅስቃሴ ያሳየ ተቋም እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን በቀጣይ ተቋሙ የሰው ሀይል አደረጃጀት፤በሶስት ዙር የሚከናወነውን ሪፎርም መተግበሪያዎች ማለትም ከግንቦት 16 እስከ ነሀሴ 16 የ10 ተቋማት ፤ከነሀሴ 16 እስከ ህዳር 16 የ20 ተቋማት፤ ከህዳር 16 እስከ የካቲት 16 የቀሩ ተቋማትን የሚጠናቀቅበት ጊዜ መሆኑን የተጠቆመ ሲሆን ፤የሰራተኞች ፋይል ዲጂታላይዝድ መደረግ እንዳለበት ፤የሰው ሀይል መጠኑ በደንብ መታየት እንዳለበት በሪፖርት ግምገማው ላይ ለተቋሙ ግብአት እንዲሆኑ ታስበው የተሰጡ አስተያየቶች ናቸው፡፡
    ከዚህም በተጨማሪ በአስተዳደሩ ያሉ የመንግስት ሰራተኞች 85 ፐርሰንት ለህጉና ለደንቡ ተገዥ ሲሆኑ 15 ፐርሰንት ለህጉና ለደንቡ የመገዛት ላይ ክፍተት ስላለ ይህ በሪፎርሙ በደንብ ተፈትሾ በ2015 ሰውን በውክልና የማሰራት ልምዳችን ከፍ ማለት አለበት የስራ ክፍተቶች መኖር የለበትም ተብሏል፡፡
    የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ እየተገበረ ያለውን ሪፎርም በማጠናከር በገጠር ላይ ያሉ ባለሞያዎች ሁሉም ስራ ላይ መሆናቸውን የመከታተል ስራ አጠናክሮ መስራት እንዳለበት ተገልጻል፡፡
    የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት ቢሮ ቀደም ብሎ ለ4 ተከታታይ ወራት የሪፎርም ስራ ተሰርቶ ተጠናቆ ወደ ስራ የገባ ቢሆንም ለውጡ ቀጣይነት እንዲኖረው በየሳምንቱ ማክሰኞ ተቋሙ እየተገመገመ ያለበት ሁኔታ መኖሩንና የሪፎርም ስራውን ተቋሙ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገልጻል፡፡
    የመንግስት ኮሚኒኬሽንና ጉዳዮች ቢሮ በተመለከተ ተቋሙ ባቀረበው ሪፖርት ግምገማ የሚዲያዎች የሰአት አከባበር ላይ በሰአቱ ቦታው አለመድረስ ክፍተት በመኖሩ ተቋሙ እንዲያስተካክልና ተቋሙ የጀመረውን ሪፎርም ስራ በማጠናከር እንዳለበት ተገልፃል፡፡
    የግምገማውን መድረክ የመሩት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ በቀረቡት ሪፖርት ላይ አስተያየት የሰጡ ሲሆን ለተቋማቱም በከተማ ቀበሌዎች ያሉ መሰረተ ልማቶች ፍታዊነታቸው ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እያንዳንዱ መሰረተ ልማቶች እንዲፈተሹ ትዕዛዝ በመስጠት የተሰጡ አስተያቶችን እንደ ግብአት በመጠቀም የ2015 በጀት አመት የዝግጅት ምዕራፍ እቅድ ጥራት ባለው ሁኔታ እንዲዘጋጅ አቅጣጫ በማስቀመጥ የ2015 በጀት አመት ለተሻለ አፈፃፀም በትጋት እንዲሰሩ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
    የአስተዳደሩ ምክትል ከኒትባ አቶ ሀርቢ ቡህ በሪፖርት ግምገማው የቀረቡት ተግባራት አፈፃፀም በቀረበው ልክ ተከናውነዋል የሚለውን ለመመልከት የድሬደዋ ምክር ቤት ፣የብልፅግና ጽ/ቤት ፣ የሱፐርቨዥን ስራ በማከናወን ስራውን የሚፈተሸ መሆኑ ተናግረዋል፡፡