ታላቁ የኢትዮጵያውያን የህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ በክፍለ አህጉሩ ያላትን ተሰሚነትና ተጽአኖ ፈጣሪነት በማሳደግ በኩል አስተማማኝ መሰረት መጣል የቻለ የኢትዮጵያውያን የጋራ ሃብት ነው

    አገራችን በተፈሰሱ አገራት መካከል የጋራ ተጠቃሚነት መኖር አለበት በሚል የራሷን ብቻ ሳይሆን ከጎረቤት ሃገራት ጋር በጋር የተጠቃሚነት መርህ ላይ የቆመ ግንኙነት ጭምር በመመስረት የነበረውን የጥርጣሬ መንፈስ በማስወገድ በኢትዮጵያ ላይ እምነት እንዲያሳድሩና ኢትዮጵያን በማግለል ለመፈታት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ፍፁም የተሳሳተ መሆኑን በጽኑ አቋማ ለማሳየት ችላለች፡፡
    ዛሬ ላይ ግድባችን በመንግስትና በህዝብ የተቀናጀ ትብብር ወደ ሶስተኛው የሙሌት ደረጃ ተሸጋግሯል፡፡ ግድባችን መሃንዲሱም፣ ግንበኛውም፣ የገንዘብ ምንጩም ከኢትዮጵያውን ሃብት ሆኖ ፍሬውን ለማየት በቅተናል፡፡ አሁን የህዳሴ ግድብ የድህነት መውጫ መንገዳችን በመሆኑ እንደ ዓይን ብሌናችን እየተንከባከብን እስከመጨረሻው ዳር ለማደረስ ማድረጋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡