የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከሲዲሲ ፕሮግረም ጋር በመተባበር ለሚዲያ ባለሞያዎች በኢች አይ ቪ ኤድስ ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገ የግንዛቤ መስጫ መድረክ አካሄዷል፡፡
ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማትና ከአስተዳደሩ መንግስት ኮሙኒዩኬሽን ቢሮ ለተውጣጡ ጋዜጠኞች በተዘጋጀው በዚሁ የግንዛቤ መስጫ መድረክ ላይ በቸልታ እየታየ ያለውንና ነገር ግን የመስፋፋት ምልክቶችን እያሳየ ያለውን ኤች አይ ቪ ኤድስን የሚዲያ ተቋማትና ጋዜጠኞች ለህብረተሰቡ የግንዛቤ መስጫ ፕሮግራሞችን እና ማስታወቂያዎችን በመስራትና በማስተላለፍ ቫረሱን መከላከልና መግታት እንደሚገባቸው ተጠቁሟል፡፡
የሚዲያ ባለሞያዎቹ ህብረተሰቡ የኤች አይ ቪ ምርመራን በማድግ እራሱን በማወቅ ከቫይረሱ ነፃ የሆነ እራሱን በመጠበቅ ቫይረሱ በደሙ የተገኘበት ደግሞ ጊዜ ሳያጠፋ የህክምና ክትትል የማድረግና መድሃኒቱን በፍጥነት መጀመር እንዳለበት የሚያስገነዝቡ ፕሮግራሞችን በየሚዲዎቻቸው በተለያየ መንገድ ሊያስተላልፉ እንደሚገባ የስልጠናው አስተባባሪዎች ተናግረወዋል፡፡
በመድረኩ የተሳተፉት የሚዲያ ባለሞያዎች በበኩላቸው በመድረኩ የቀረቡት ፅሁፎች በኤች ኤ ቪ ኤድስ ቫይረስ ዙሪያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እንዲገነዘቡ ያደረጋቸው ከመሆኑም ባሻገር ለቀጣይ በጉዳዩ ዙሪ ያለሚሠሯው ሥራዎች ግብዓት እንደሚሆናቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የበሽታ መከላልና መቆጣጠር ኬዝ ቲም አስተባባሪ የሆኑት አቶ ጅሃድአባ ነጋሽ አባገሮ በበኩላቸው በኤች አይ ቪ ኤድስም ሆነ በሌሎች ጤና ነክ ጉዳዮች ላይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤን ከመፍጠር አንፃር አብረውን ሊሠሩ የሚችሉና እየሠሩ ያሉ በርካታ የሚዲያ አካላት ስላሉን ዕድለኞች ነን ያሉ ሲሆን ሚዲያዎች በኤች ኤ ቪ ኤድስ መከላከልና መግታት ዙሪያ ህብረተሰቡን ለማስተማር በምትሠሯቸው ፕሮግራሞችም ሆነ ሌሎች ዝግጅቶች ትኩረት ልታደርጉባቸው የሚገባ ጉዳዮችንና ፕሮግራሞቻችሁን የምታስተላልፉባቸውን ጊዜያት መለየት፤ ማህበራዊ ድረ-ገፆቻችሁን ጨምሮ በየትኛው የማስተላለፊያ ዘዴዎች መሥራት እንደሚገባችሁ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት መመካከር እንደሚገባና በጋራ ሆነን ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከልና ብሎም ለመግታት ተግተን ልንሠራ ይገባል ብለዋል፡፡


