የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

    1. መግቢያ
    በየደረጃው የሚሰጠው ትምህርት ሀገሪቱ ለተያያዘችው የዲሞክራሲ ሥርአት ግንባታ፣ የመልካም አስተዳዳር
    መስፈንና ለልማት ቁልፍ አስተዋጽኦ የሚያበረክት፣ በየደረጃው የሰለጠነ፣ በቂ እውቀት፣ ክህሎትና መልካም
    ሥነምግባር ተላብሶ የሀገር ልማትን ለማፋጠን በቁርጠኝነት የሚሰራ ዜጋ ለማፍራት የሚያስችል መሆን ይኖርበታል፡፡
    ይህን እውን ለማድረግ የሚያስችልና አገራችን መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ እንዲትሰለፍ የሚያስችል
    የትምህርት ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት እና የትምህርት ፍኖተ ካርታውን መሰረት በማድረግ የአስር አመት መሪ እቅድ
    በማዘጋጀት ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡ ለዚህ እቅድ ስኬታማነት የሚያስፈልገውን ብቁ የሰውሃይል
    በማፍራት የትምህርት ሴክተር ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ በመሆኑም በትምህርት ዘመኑ በፈጠርነው ምቹ ሁኔታ የታዩ
    በጎ ጅምሮችን በማጠናከርና መልካም ተሞክሮዎች በማስፋፋት እንዲሁም የለየናቸውን ችግሮች በመፍታት በዘርፉ
    ማእከላዊ ተልእኳችን የሆነውን የትምህርት ጥራት የማጐልበትሥራ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡
    ይህ የትምህርትና ስልጠና ሂደት በእቅድና ፕሮግራም የሚመራ ስለሆነ የትምህርት ዘርፍ ልማት ፕሮግራም የትኩረት
    አቅጣጫና አላማ መሰረት በማድረግ ስድስተኛው የልማት የአምስት አመት እቅድ ተዘጋጅቷል፡፡ እቅዱ የትምህርት
    ጥራት ለማስጠበቅ ያስችለን ዘንድ በፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር በተቀረፀው የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት
    ማረጋገጫ ፓኬጅን መሰረት በማድረግ ከዚህ ቀደም ከተሰሩት የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ ታስቦ ተዘጋጅቷል፡፡
    በመሆኑም ይህ 2014 በጀት አመት የ 3ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የቢሮውን ራዕይ፣ ተልዕኮና የጋራ የሆኑ
    እሴቶችን ያካተተ ሲሆን የአገር አቀፉን የትምህርት ፍኖተካርታ አላማ እና ፕሮግራም፣ ከመስተዳደሩ ተጨባጭ ሁኔታ
    የተጣጣመውን እቅድ እና የቢሮው የሚዛናዊ ውጤት ተኮር እቅድ መሰረት አድርጎ በዋና የስራ ሂደቶች በሚከናወኑ
    ግብ ተኮር ተግባራት ስር የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም ነው፡:………….የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 በጀት ዓመት የመደበኛ ስራዎች የ 3ኛ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት