በትላንትናው ዕለት መካሄድ የጀመረው በ2014 በጀት ዓመትበ1,2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውና በገጠርና በከተማ ተሰርተው የተጠናቀቁ 31 የልማት ፕሮጀክቶች የምርቃት ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለትም በገጠር ክላስተር ቀጥሏል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ የተሳተፉ ሉዑካን ቡድን የአስተዳደሩ ከንቲባ የተከበሩ ከድር ጆሀር የመሩ ሲሆን በአሰሊሶ ክላስተርና በለገኦዳ ጉዱንፈታ አነስተኛ መስኖ ፣በሁሉል ሞጆ የግድብና የካናል፣የሀሎ ቡሳና ለጎኦዳ ሚርጋ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች እንዲሁም በማህበራዊ ዘረፉ የአሰሊሶ ክላስተር የ2ኛ ደረጃ ትምህረት ቤት የምርቃት ስነ ስረአት ተከናውኗል።
የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጆሀር በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ እንደተናገሩት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን በቀጣይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ተሰርተው እንደሚጠናቀቁ ገልፀዋል ፡፡
የተጠናቀቁ የልማት ፕሮጀክቶችን የአስተዳደሩ ነዋሪዋች በባለቤትነት ተረክቦ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጡ የበኩላቸውን አስተወጽኦ እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፋዋል።
በልማት ስራው ተጠቃሚ የሆኑ የአካባቢው ነዋሪዋችም ቀደም ብሎ ውሀና ትምህርት ፍለጋ እራቅ ወዳለ ቦታ ሄደው አገልግሎቱን እንደሚያገኙ የተናገሩ ሲሆን ይህን አገልግሎት በአካባቢያቸው በማግኘታቸው ጊዜንና ልፉታቸውን እንደሚቀንስ በመግለፅ የመስኖ ውሀ በማግኘታቸው ምርታቸው እንደጨመረና የተሻለ ገቢ ማግኘት መጀመራቸውን ገልፀዋል።
በነገው እለትም በገጠር የቀሩ የልማት ፕሮጀክቶች ይመረቃሉ


