በድሬዳዋ አስተዳደር የአቅመ ደካማ ቤቶችን የማደስ ስነ-ስርአትን ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች አስጀመሩ ።

    በድሬዳዋ አስተዳደር ላይ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ለሚኖሩ አቅመ ደካማ የሆኑ እናቶችና አባቶች የሚኖሩባቸውን ቤቶች ከዚህ ቀደም በየአመቱ በክረምት ወራት የበጎ-ፍቃድ ስራዎች ላይ ቤቶቹን አፍርሶ የማደስ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል ።
    በዛሬው እለትም በከተማዋ ላይ የሚኖሩና በአቅም ማነስ ምክንያት በደሳሳ ጎጆ ውስጥ የሚኖሩ አቅመ ደካማ የሆኑ እናቶችና አባቶች ቤቶችን አፍርሶ የማደስ መርሀ-ግብርን ከፍተኛ የአስተዳደሩና የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች አስጀምረውታል ።
    በዛሬው እለትም በአስተዳደሩ ላይ አቅመ ደካማ የሆኑ ዜጎች የሚኖሩባቸውን ቤቶች አፍርሶ የማደስ መርሀ-ግብር የተጀመረውም በ 05 ፣ በ 07 እንዲሁም በ 08 ቀበሌዎች ላይ ሲሆን የዚሁ መርሀ-ግብር ተጠቃሚ የሆኑ አካላትም ለረጅም አመታት በደሳሳ ጎጆ ቤት ውስጥ በመኖራቸው ምክንያት ለከፋ ችግር ተጋላጭ ሆነው መቆየታቸውን ተናግረው አሁን ላይም ቤታቸው ለመታደስ እንቅስቃሴ በመጀመሩ እንዳስደሰታቸውም ተናግረዋል ።
    በዚሁ ስነ-ስርአት ላይም አቅመ-ደካማ ለሆኑ ዜጎች የምግብ ፍጆታ ድጋፍም ተደርጓል ።