በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደው 18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዎና ተሳታፊ የሆነችው ሀገራችን ኢትዮጵያ 4 የወርቅ 4 የብር 2 የነሃስ በድምሩ 10 ሚዳልያ በማግኘት ከአፍሪካ 1ኛ ከአለም ደግሞ ሁለተኛ ድረጃን በማግኘት አክሪ ድል ያስመዘገበች ሲሆን የዚህ አኩሪ ድል ባለቤት የሆኑት አትሌቶቻችን እና የዘርፉ አሰልጣኞች እና አመራሮች ከድል በኋላ ወደ ሀገር ቤት ሲመለሱ ደማቅ የሆነ የጀግና አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
ከዚህም ባለፈ መንግስት እንደሀገር በበርካታ ችግሮች ውስጥ እያለንም ቢሆን አሸናፊ መሆናችንን ያሳየ እና ለጠላቶቻችን ደግሞ ተስፋን የሚያስቆርጥ ድል በመሆኑ በዛሬው እለት በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤት አመራሮች እና ሠራተኞች በሙሉ ይህን አኩሪ ድል ላሰመዘገቡ ጀግና አትሌቶቻችን ምስጋና እንዲያቀርቡ አቅታጫ መቀመጡን ተከትሎ የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ፣የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ፍትሕ ፀጥታና ሕግ ጉዳዮች ቢሮ አመራሮች እና ሠራተኞች በጋራ በመሆን ‹‹ አንድ ሆነን እንስራ ኢትዮጵያ ታሸንፍ !!!›› በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በምስጋና ፕሮግራሙ ላይ የተገኙ የ3ቱ ተቋማት አመራሮች ባስተላለፉት መልዕክ በአትሌቲክሱ ዘርፍ የተገኘው ድል ከስፖርትም ባለፈ እንደገሀር ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት መሆኑን ገልፀው ይህም እንደሀገር በብዙ ፈተናዎች ውስጥም ሆነን አንድነታችንን ካፀናን ብሎም ከተባበርን የማናልፈው ፈተና እንደሌለና ሁሌም አሸናፊ መሆናችንን ያሳየንበት አጋጣሚ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ከዚህም ባለፈ ሁሉም የተቋማቱ ሠራተኞች በተሰማሩበት የሞያ ዘርፍ በጋራ ጠንክረው በመስራት እትዮጵያን የምንጊዜም አሸናፊ ሀገር ለማድረግ በትጋት እንዲሰሩም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡


