በዋሂል ክላስተር የህዝብ ተመራጮች ከነዋሪው ጋር ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ

    በመድረኩ በክላስተሩ ያሉ 9 ቀበሌዎች የተውጣጡ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ሲሆን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድሬደዋን ከወከሉት ሁለት ተወካዮች አንዱ የሆኑት የተከበሩ አቶ አብዱጁሃድ መሃመድ በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በድሬደዋ ደረጃ የተከናወኑ የልማት ስራዎች እንዲሁም ያሉ ችግሮችን ለነዋሪው ማብራሪያ አድርገዋል።
    የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ከሪማ አሊን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ሃላፊዎች በመድረኩ ተገኝተዋል ።
    ሙሉ ዘገባውን ተከታትለን የምናደርስ ይሆናል።