በአስተዳደር ደረጃ በየአመቱ በሚከናወነው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ለመሳተፍ የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እና የቢሮው ተጠሪ ተቋም የሆነው ድሬዳዋ ሥራ አመራርና ካይዘን ኢንስቲትዩት አመራሮች አና ሠራተኞች የአንድ አቅመ ደካማን ቤት ለማደስ ወስነው የቤት እድሳቱን ስራ የሚያስተባብር ኮሚቴ በአስተዳደር ደረጃ በዚህ ክረምት ለእድሳት ከተመረጡ ቤቶች መካከል አንዱ የሆነውን በ01 ቀበሌ የሚገኘውን የወ/ሮ አሁዳ ጅብሪልን ቤት ከሁለት ቀናት በፊት መረከባቸው የሚታወስ ነው።
በዛሬው እለትም የቤቱ የተጀመረ ሲሆን በእድሳት ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩም በብልፅግና ፖርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የወጣቶች ሊግ ኃላፊ ተወካይ እና የሊጉ የፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወጣት ፈልመታ መሀመድ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ተወካይ እና የድሬዳዋ ሥራ አመራርና ካይዘን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አወቀ ለገሰ፣ የቢሮው የለውጥ ስራዎች ጥናት፣ክትትል እና ግምገማ ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘለቀ አባተ፣ የቢሮው የመልካም አስተዳደር ችግሮች ጥናት፣ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግርማ ዘለቀ እና የቢሮው ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
በጎነት ለራስ ነው!!!!


