# 🇪🇹 ነሀሴ 28/2014 በድሬዳዋ አስተዳደር “ለሀገር ክብር በትግል እናብር” በሚል መሪ ሀሳብ በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ የሴቶች የውይይት መድረክ ተካሄደ።

    በዛሬው እለት በድሬደዋ አሰተዳደር በሃገራዊ ወቅታው ጉዳይ የሴቶች ውይይት መድረክ ላይ ሴቶች አሸባሪው የህወሃት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ለ3ኛ ጊዜ የከፈተውን ጦርነት በማውገዝ በሁሉም ዘርፍ ከመከላከያችን ጎን በመሆን አሰፈላጊዉን ድጋፍ በማድረግ ዝግጁ መሆናችውን አስታውቀዋል።
    አሸባሪው ህወሃት በተደጋጋሚ በከፈተው ጦርነት በርካታ ሴቶችና ህጻናትን ኢሰብአዊ ድርጊት ከመፈጸም ባለፈ በርካታ ንብረቶችን እያወደመ መሆኑ የሴቶች ሊግ ድርጊቱን የሚያወግዘው መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ሴቶች ሊግ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሁክሚያ መሀመድ ተናግረዋል።
    በተደጋጋሚ በመንግስት በኩል የተሰጠውን የሰላም ጥሪ ወደ ጎን በማለት በጀመረው ጦርነት እየደረሰ ያለውን ታሪክ የማይረሳው የእናቶች፣ ህጻናትና ሴቶች ላይ የሚያደርሰውን ሁሉን አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አውቆ እንዲያወግዝም የአስተዳደሩ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ጫልቱ ሁሴን ጠይቀዋል።
    አሸባሪው የህወሓት ቡድን በትግራይ እናቶችና ህጻናት ላይ እያደረሰ ያለው ኢሰብአዊ ድርጊት አልበቃ ብሎት ለ3ኛ ጊዜ የከፈተብንን ጦርነት በማውገዝ ከሰራዊቱ ጎን ለመቆም መዘጋጀታቸውን የአስተዳደሩ ሴት አደረጃጀት አባላት በውይይት ላይ አንስተው የጋራ መግባባት በመፍጠር ውይይቱ ተጠናቋል።
    DIREPROSPERITY