በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የድሬዳዋ አሰተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የ2015 በጀት አመት እቅድ ገምግሟል::

    በምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ በተደረገው የግምገማ መድረክ ላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አመራሮች እና ደጋፊ ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን እቅዱ በዝርዝር ከቀረበ በኋላ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
    የቢሮው 2015 በጀት አመት እቅድ የአስር እና የአምስት አመቱን እስትራቴጂክ እቅድ እንዲሁም በእስትራቴጅክ ግቦች የተከፋፈለ፣ የ2014 በጀት አመት አፈፃፀም ግምገማ ወቅት ለቢሮው የተሰጡ ግብረ መልሶችን ያማከለ እቅድ መሆኑን የምክር ቤቱ የመህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ አህመድ ሰይድ በጥንካሬ ገልፀው እንዲካተቱ አስተያየት የተሰጠባቸው ጉዳዮች ተካተው እንዲከናወን አቅጣጫ ሰጥተዋል።