ለ3ተኛ ጊዜ አሻፈረኝ ብሎ የመጣውን የጠላት ሀይል ለመመከት እየተንቀሳቀሰ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት በድሬደዋ አስተዳደር የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት የስንቅ ዝግጅት እና ደም ልገሳ መርሀግብር አካሂደዋል፡፡
በመርሀግብሩ ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ እንደተናገሩት እንደሀገር ሰላማችን እንዲረጋገጥ በግንባር የሚገኘውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት መደገፍ ሀገራዊ የውዴታ ግዴታችን ነው ያሉ ሲሆን እንደ እንደተቋምም ይህንኑ ሀገራዊ ግዴታችንን ለመወጣት በተለያዩ ጊዜያት ድጋፎችን አድርገናል የእለቱም የስንቅ ዝግጅት ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን ነን ለማለት ያህል የተዘጋጀ መርሀግብር ነው ብለዋል፡፡
ከዚሁ ጎን ለጎንም አመራሩ እና ሰራተኛው ተሰባስቦ በመወሰን ከደሞዛቸው ተቆራጭ በማድረግ ገቢ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ እንዳለ ተናግረዋል፡፡
ሁሉም ቢሆን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ሚያደርገውን ድጋፍ በማጠናከር ደጀንነቱን እንዲያስመሰክርም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የደም ልገሳውም በደም እጦት ሚሞቱ ዜጎችን ለማገዝ ተሳቢ በማድረግ ከድሬደዋ ጤና ቢሮ ደም ባንክ ጋር በመቀናጀት መከናወኑ ተጠቁሟል፡፡መረጃው የድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ባለስልጣን ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው


