የድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ባለስልጣን የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ት/ቤቶችን በማስተባበር እና በራሱ ወጭ የገዛቸውን 200ሺ ብር ሚገመት የትምሀርት ቁሳቁስ ግብአት ለድሬደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስረክቧል፡፡

    ድጋፉ ታዳጊዎች በትምህርት ግብአት ችግር ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ ጉልህ ድርሻ እንዳለው የገለፁት በድሬደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ ናቸው፡፡ በመሆኑም ተቋሙ በራሱ እና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶችን በማስተባበር ላደረገው ድጋፍ አመስግነው መሰል ድጋፎች ሊጠናከሩ እንደሚገባ ነው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
    ድጋፉን ያስረከቡት የድሬደዋ አስተዳደር ትራንፖርት እና ሎጂስቲክ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ በበኩላቸው ድጋፉ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ታዳጊዎች በኢኮኖሚ ችግር ሳቢያ ከትምህርት ገበታ እንዳይቀሩ ኃላፊነትን ለመወጣት የተደረገ ድጋፍ መሆኑን አውስተው በቀጣይም ይህ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
    በዚሁ ድጋፍ በአስተዳደሩ ሚገኙ የግል አሽከርካሪ ማስልጠኛ ትመህርት ቤቶች 40ሺ ብር ሚጠጋ አስተዋፆ በማድረግ ቁሳቁስን ገዝተው ሲያስረክቡ ተቋሙ በበኩሉ 147ሺ ብር በላይ ወጪ በማድረግ ከ10 ካርቶን በላይ ደብተር ገዝቶ አስረክቧል፡፡
    መረጃው የድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ባለስልጣን ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።