የትግራይ ሴት ተወላጆች ለመከላከያ ሰራዊት የስንቅ ድጋፍ ዝግጅት

    በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ ሴቶች ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት የስንቅ ዝግጅት መርሐ ግብር እያካሄዱ ነው።
    ሴት ሰላምንም ጦርነትንም የማስቆምም ሆነ የማስቀጠል ችሎታው በእጇ ነው ሲሉ በስንቅ ዝግጅቱ ተሳታፊ የሆኑ የትግራይ ሴት ተወላጆች ገልጸዋል።
    ስንቅ ማዘጋጀት ብቻም ሳይሆን በማንኛውም ቦታ እና ጊዜ ሁሉ ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመሰለፍ አሸሸባሪውን ህወሓት ለመደምሰስ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።
    ለመላው የትግራይ ህዝብ እና ተወላጅም ለርሃብ እና ለችግር የዳረገውን የሽብር ቡድን ከመከላከያ ጎን በመሰለፍ ለመጨረሻ ጊዜ ሊያስቆመው እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
    ኢቢሲ ነዉ የዘገበዉ