ድሬደዋ አስተዳደር ማህበረሰብ በምክር ቤት ውክልና አወጣጥ ውይይት ወቅት ያነሳቸው ጥያቄዎች በ2015 በጀት አመት በእቅድ እንዲካተቱ ስምምነት ላይ ተደረሰ ።

    የድሬዳዋ አሰተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የን/ኢ/ኢ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ እና የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ፈቲያ አደን በጋራ በመሆን በተመራ የውይይት መድረክ በአጠቃላይ የድሬዳዋ ህዝብ የምክር ቤት ውክልና አወጣጥ የውይይት መድረክ ወቅት በዘጠኙም ከተማ ቀበሌ እና በ38ቱ ገጠር ቀበሌዎች ህዝቡ በምክር ቤት ለወከላቸው የህዝብ እንደራሴዎች ያነሳቸውን ጥያቄዎች በመለየትና ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የፌዴራል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬደዋ አስተዳደር ተወካዬች የተከበሩ ዶ/ር ቢፍቱ መሀመድ እና የተከበሩ አቶ አብዱጁሀድ መሀመድ በተገኙበት የተነሱ አንገብጋቢ ችግሮች በመለየት
    1.በፌደራል መንግስት የሚፈቱ
    2.በድሬደዋ አስተዳደር አስፈፃሚ ተቋማት እና
    3.በድሬደዋ አስተዳደር ህዝብ የሚፈቱ ችግሮችን በመለየት አስፈፃሚ አካላት በአጭር፣በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ የሚፈቱበትን እስትራቴጂ በመቀየስ በ2015 በጀት አመት የሚፈቱትን በእቅዳቸው በማካተት ከህዝብ የተነሱ ችግሮች እንደሚፈቱ በጋራ የውይይት መድረኩ መግባባት ላይ ተደርሷል ።
    በመጨረሻም በምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ እና በድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲያ አደን በጋራ በመሆን የተመራው የውይይት መድረክ በተለይ በ2014 ዓ.ም በህዝቡ የተነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ ሚና የነበራቸው አካላት ማለትም የፌዴራል መንግስት ፣የፌዴራል ህዝብ ተወካዮ ምክር ቤት የድሬደዋ ተወካዮች፣ የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አካላት፣የድሬደዋ አስተዳደር ህዝብ፣የብልፅግና ፖርቲ ጽ/ቤት እና በየደረጃው የሚገኙ የድሬደዋ አስተዳደር አስፈፃሚ ተቋማት አመራርና ሰራተኞች ከፍተኛ ምስጋና እንደሚገባቸው እና ቀሪ ችግሮችንም በጋራ በመሆን በቀጣይ ለመፍታት እና የድሬደዋን ራዕይ እውን ለማድረግ በተጀመረው መልኩ ሁሉም ሚናውን እንዲወጣ መልዕክት በማስተላለፍ ውይይቱ ተጠናቋል ።
    የድሬደዋ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ