የድሬዳዋ መንግሰት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ ለመስቀል በአል የመልካም ምኞት መልዕክት።

    የእንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!
    መስቀል የፍቅር፣ የሰላምና የአብሮነት በዓል በመሆኑ የመስቀል ደመራ በዓል የጨለማው በብርሃን መሸነፍ ማሳያ በመሆኑ ይህንን በዓል በፍቅር፣ እርስበእርስ በመተሳሰብ ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በመስራት፣ ጀግኖችን በማክበር፣ ደጀንነትን የበለጠ በማረጋገጥ፣ አንድነትን በማጽናት እንደ ደመራው ደምቀን ጨለማ በሆነብን ሁሉ ላይ እያበራን በአሸናፊነት እንቀጥል ሲሉም መልዕክተ አስተላልፈዋል።
    የመስቀል በዓል አከባበር ልዩ የሚያደርገው መስቀል የሰላም፣ የአብሮነት፣ የመተሳሰብ፣ የመደጋገፍ፣ የመከባበር ከመሆኑም ባሻገር የድሬዳዋ እሴታችን ደምቆ የሚታይበት በዓል ነው ብለዋል፡፡
    ህብረተሰቡ የተለመደ የመተዛዘንና የመረዳዳት ባህሉንም በመተግበር በዓሉን ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር እንዲያከብርም ጥሪ አቅርበዋል።
    የተጀመረው የእድገት እና የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን በየአካባቢያችን ሰላማችንን አጽንተን ያሉንን ጸጋዎች በመጠቀም ሙሉ አቅማችንን እና ትኩረታችንን በልማት ላይ ልናደርግ ይገባል ብለዋል።
    በድጋሚ እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን።
    የድሬዳዋ መንግሰት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ