የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጥሪን ተከትሎ ወደ ሃገር ቤት የገቡና በድሬዳዋ የሚገኙ ዲያስፖራዎች በአስተዳደሩ የሚገኙ የተለያዩ ግዙፍ የልማናት ስራዎችን እንዲጎበኙ ተደርጓል።
በተለያዩ የውጭ አገራት ኑሯቸውን ያደረጉና ድሬዳዋ የሚገኙ ዲያስፖራዎች የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ዞንና የነፃ የንግድ ቀጠና ዞን ጎብኝተዋል።በጉብኙቱ ዲያስፖራውን በልማት ስራ እንዲሰማሩ የሚያነሳሳ ስራ መኖሩን መመልከታቸውን ያነጋገርናቸው ዲያስፖራዎች ገልፀውልናል።
ቀደም ሲል ኑሯቸውን በባህር ማዶ አድርገው የነበሩ አሁን በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ስራ ላይ የሚገኙ ባለሃብቶች ተሞክሮ በጉብኝቱ ታይቷል።የነዚህ ባለሃብቶች የስራ እንቅስቃሴ በቀጣይ እነሱም በአገራቸው ሰርተው ማትረፍ እንደሚችሉ ያመላከተ እንደነበር በጉብኝቱ የተሳተፉ ዲያስፖራዎች ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ወደብና ተርሚናል የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ደረቅ ወደብ የስራ እንቅስቃሴ፣የድሬዳዋ ሙዚየም፣የባቡር ሽርሽር መርሀ ግብሮች የጉብኝቱ መርሃ ግብሩ አካል የነበረ ሲሆን በአጠቃላይ ጉብኝቱ የድሬዳዋን ታሪክ ብሎም አስተዳደሩ ለልማት ያለውን አቅም በቂ ግንዘቤ እንዲጨብጡ ያስቻላቸው እንደነበር ዲያስፖራዎቹ ገልፀዋል።


