የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም የ 2016 ዓ.ም የመጀመሪያው ግማሽ አመት እቅድ አፈፃፀምን ገምግሟል

የድሬ ብድርና ቁጠባ ተቋም ባለፉት አመታት በተለይም በድሬዳዋ አስተዳደር በከተማም ሆነ በገጠር ለሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የብድርና የቁጠባ አገልግሎት ፣ እንዲሁም ዘርፈ-ብዙ ኢኮኖሚያዊ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ፡፡ ተቋሙ በድሬዳዋ ፣ በሀረር እንዲሁም ደግሞ በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጂጂጋ ቅርንጫፎችን በመክፈት ፈጣን አገልግሎቶችን ለነዋሪው ህብረተሰብ እየሰጠ ሲሆን በዛሬው እለትም የተቋሙ የ 2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ገምግሟል ።

በተለይም የድሬ ብድርና ቁጠባ ተቋም በጀት አመቱ በቁጠባ እና በብድር ስርጭር ላይ እቅዱን በቦርድ በማፀደቅ ወደ ስራ የገባ ሲሆን በግማሽ አመቱ ቁጠባን ከማሰባሰብ አኳያ 317,858,910.00 ቁጠባ ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 674,683,564.00 ብር የተሰበሰበ ሲሆን ይህም የዕቅዱን 212 % መፈፀም መቻሉን ነው የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ተሾመ አበበ ያስታወቁት ።

ከብድር አፈፃፀም ጋር ተያይዞ በበጀት ዓመቱ ለ 1 ሺህ 860 የብድር ደንበኞች ብድር ለማሰራጨት ታቅዶ ለ 1 ሺህ 722 የብድር ደንበኞች ማፍራት የተቻለ ሲሆን ይህም የዕቅዱን 92.58 % ማሳካት ተችሏል ። በብር በግማሽ በጀት ዓመቱ በድምሩ 302,303,431.00 ብር ለማበደር ታቅዶ 323,672,346.00 ብርም ማበደር የተቻለ ሲሆን ይህም የዕቅዱን 107 % መፈፀም መቻሉም ተገልፆል ፡፡

ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ብድር አፈፃፀምን በተመለከተ በ 2016 ዓ.ም የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ 1 ሺህ 540 የሚሆኑ ኢንተርፕርነሮች ለማበደር ታቅዱ 1 ሺህ 337 ማበደር የተቻለ ሲሆን ይህም የዕቅዱን 87 % መፈፀም ተችሏል ፡፡ በብር ደግሞ በግማሽ ዓመቱ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ ኢንተርፕርነሮች ብር 271,845,331.00 ለማበደር ታቅዶ ብር 276,161,346.00 የተሰራጨ ሲሆን ይህም የዕቅዱን 102 % መፈፀም ተችሏል ።

ብድር አመላለስን በተመለከተ በ 2016 ዓ.ም ግማሽ ዓመት 129,212,331 ብር ብድር ለመሰብሰብ ታቅዶ 124,758,404 ብር መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን ይህም የዕቅዱን 97 % ማከናወን መቻሉን የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ተሾመ አበበ አስታውቀዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *