የኮሚዩኒኬሽንና የተግባቦት ስራው ቴክኖሎጂን መሰረት ባደረገ ዘመናዊ መንገድ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
የድሬደዋ አስተዳደር ምክርቤት የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአስተዳደሩን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የ2016 ዓም የስድስት ወራት አጠቃላይ የስራ እንእስቃሴ ገምግሟል፡፡
በቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ጫልቱ ሁሴን የተመራው የድሬደዋ አስተዳደር ምክርቤት የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቢሮው በነበረው ቆይታ ከአሰራር አደረጃጀትና ከትግበራ አንፃር ያሉ ጠንካራና ሊሻሻሉ የሚገባቸውን ጉዳች አንስቶ ከቢሮ ሃላፊው አቶ ብሩክ ፈለቀ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡
ቢሮው በተለይም አዳዲስና ዘመናዊ ሶፍትዎሮችን በማበልፅግ አሰራሩን ለማዘመን የሄደበት እርቀት ቀልጣፋና ውጤታማ ስራን ለማስመዝገብ እያስቻለው እንደሚገኝ በወቅቱ ተገልጿል፡፡የሰራተኞችን አቅም ለማጎልበት ተጠናክሮ ማስቀጠል የሚገባ ስራ መሆኑንም ተመላክቷል፡፡
በቢሮ ውስጥም ሆነ ከቢሮው ውጪ የሚከናወኑ የበጎ አድራጎት ስራ በተሞክሮነት የሚጠቀስ ተግባር መሆኑም በውይይቱ ተጠቁሟል፡፡ከአደረጃጀትና የሰው ሃይል ማሟላት እንዲም ሌሎች እንቅፋት የሚሆኑ ጉዳዮችን ቀርፎ በቀጣይ ጊዜ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ መሰራት እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
ቢሮው በተለያዩ መንገዶች የድሬዳዋን ገፅታ ለመገንባት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች በቋሚ ኮሚቴው የተጎበኙ ሲሆን የተለያዩ አካላትን በማስተባበር የሚሰሩ ስራዎች በበጀት በተደገፈ መልኩ ሊተገበሩ እንደሚገባቸው በቋሚ ኮሚቴው ተገልጿል፡፡


