በአነስተኛ የአምራች ዘርፎች የተሰማሩ አንቀሳቃሾችን መደገፍ ውጤታማ እንዲሆኑ እንደሚያግዝ ተገለጸፀ።

በአስተዳደሩ በአነስተኛኛ መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ የሳሙና ምርት ላይ ለተሰማሩ አንቀሳቃሾችን የምርትናምርታማነትን አቅም ለመጨመር የሚያስችል ስልጠና እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በትላልቅ ደረጃ የሚጠቀሱ ግዙፍ የማኒፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችን ላማስፋፋት በቅድሚያ ለአነስተኛና መካከለኛ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በቂ ትኩረት በመስጠ እንደሚገባ ቻይናና ህንድን ጨምሮ በአለም ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት ያላቸውን አገራት ተሞክሮ ያሳየናል፡፡

እነዚ አገራት ለአነስተኛና መካከለኛ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ጭምር ለምርት የሚያስፈልጉ ግብአቶችን እንዲያቀርቡ የሚያስችል የገበያ ትስስር የሚፈጥሩበት ሁኔታ በስፋት ይታያል፡፡

በድሬደዋ እንደ አገር ለዘርፉ የተሰጠውን ትኩረት መሰረት በማድረግ የተለያዩ የድጋፍና ክትትል ስራዎች ይከናወናሉ፡፡ በአስተዳደሩ ላሉ 14 የሳሙና አምራች አነስተኛና መካከለኛ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች እየተሰጠ የሚገኝው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዘርፉ ከሚከናወኑ የድጋፍና ክትትል ስረዎች አንዱ ነው፡፡

ስልጠናው የስራ ክህሎትን በማሳደግ ምርታማነትን ለመጨመር የሚረዳ እንደሆነ የስልጠናው ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡የሂሳብ አያያዝና አስተዳደር፤የገበያ መዳረሻን በማስፋ ተወዳዳሪነትንና ትርፋማነትን ከፍ ማድረግ የሚያስችሉ አሰራሮችን የተመለከቱ ሃሳቦች በስልጠናው ተካተዋል፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *