#DGC የካቲት 24/2016
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እና ካቢኔያቸው፥ በአዲስ አበባ የተገነቡ ህብረተሰብ ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
ቡድኑ ተዘዋውሮ ከጎበኛቸው የልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ ተስፋ ብርሀን የምገባ ፕሮግራም፥ የሴቶች ማበልፀጊያ ማዕከል እንዲሁም የለሚ የእንጀራ ማምረቻ ፋብሪካ ፣ የአረንጓዴ ልማትን እና ሌሎች ፕሮጀክቶች ይገኙባቸዋል።
ካቢኔው በአጭር ግዜ ተሰርቶ የተጠናቀቀውን የአድዋ መታሰቢያ ሙዝዬምን የጎበኘ ሲሆን፥ ከንቲባ ከድር ጁሀር ይህ ፕሮጀክት ቁርጠኝነት እና በሳል አመራር የታየበት ነው ሲሉ ገልፀዋል።
በጉብኝቱ እና ልምድ ልውውጡ የተገኙ ተሞክሮዎችንም በመቀመር የተመረጡ ፕሮጀክቶችን ወደ ተግባር እንደሚያስገቡም ከንቲባው አስታውቀዋል።


