የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ጋር የነበራቸውን ቆይታ አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ የትስስር ገፃቸው የሚከተለውን መልዕክት አስተልምለፏል።

በአዲስ አበባ ቆይታችን ፥ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ለመስራት ከተፈራረምነው የእህት ከተሞች ስምምነት ባሻገር ፥ ሰው ተኮር በሆኑ የልማት ፕሮጀክቶች ጉብኝት የአመራር ሰጪነት ሚናችንን ለማጎልበት የሚረዱ ግብዓቶችን አግኝተናል።

የአስተዳደራችን ካቢኔ በቀጣይ፥ በስማርት ሲቲ፥ በተቋማት ሪፎርም ትግበራ እና ምገባ ፕሮግራም፥ እንዲሁም በካፒታል ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ዙሪያ ያገኘውን ልምድና ተሞክሮ ወደ መሬት በማውረድ፥ ለድሬዳዋችን ሁለንተናዊ እድገት በይበልጥ እንደሚተጋ አምናለሁ። በርቱ እንበረታለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *