የድሬዳዋ አስተዳደር 128ኛው የአድዋ ድል በዓል ድሉን በሚመጥን መልኩ በተለያዩ ሁነቶች በከንቲባ ጽ/ቤት አዳራሽ በርካታ ታዳሚያን በተገኙበት በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል ።
የአድዋ የድል በዓል የመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራት፣ ጀግንነት ፣የፍቅር የአንድነት ማሳያ የድል በዓል ነዉ።
አድዋን በሚዘክረው በዚሁ የድል በዓልም የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ ጨምሮ የአስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ሴቶች፣ወጣቶች ተገኝተዋል።
ከበዓሉ አከባበር ጋር በተያያዘ ያሉትን ሁነቶች ተከታትለን ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል።


