#ዜና በድሬዳዋ አስተዳደር አለም አቀፍ የሴቶች ቀን የማጠቃለያ መድረክ ተካሄደ

‘ሴቶችን እናብቃ፤ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ!” በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ113ኛ በኢትዮጵያ ለ48ኛ ጊዜ የሚከበረው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን (mARCH 8)የማጠቃለያ መድረክ በድሬዳዋ አአስተዳደር ተካሄደ ።

ቀኑን አስመልክቶ በተዘጋጀው መድረክ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ ከድር ጆሀር ባስተላለፉት መልዕክት ሴቶች በሀገራች በተሰጣቸው የኃላፉነት ቦታ ሁሉ ውጤትን በማስመዝገብ በብቃትና በብልሀት የተሰጣቸውን ኃላፊነት የሚወጡ ናቸው ብለዋል።

ክቡር ከንቲባ ከዚህም ጋር አያይዘው ሴቶችን ወደ አመራርነት ለማምጣት በአስተዳደሩ ያሉ ሴት አመራሮች የድርሻቸውን እንዲወጡ መልዕክት በማስተላለፍ ለዚህም አስተዳደሩ በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ሁሉ ከጎናችሁ ነውም ብለዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ፈትያ አደን በመድረኩ ላያ ባደረጉት ንግግር ባለፉት ጊዜያት ሴቶች በተለያዩ ስራዋች ከወንዶች እኩል ተሳትፎ እንዳይኖራቸው፣እንዳይማሩ በአደባባይ ወተው የመናገርም ሆነ የመስራት መብታቸው ተጥሶ በኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካው እንዲሁም በአመራር ሰጪነት ላይ ሊኖራቸው የሚገባውን ሚና ተሳትፎ ተነፍገው በማህበረሰቡ እድገት ውስጥ ምንም አይነት አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ አይችሉም በሚል ኋላቀር አስተሳሰብ ቦታ ሳይሰጣቸው ቆይቷል ብለዋል።

ይህን ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት በተለያዩ ዘርፎች በፆታ መካከል የሚታዩ የመብት ልዩነቶችን ለማስቀረት የሚያግዙ ቤሄራዊ መዋቅሮች ለማጠናከር በርካታ ጥረቶች ተደርገዋልም ብለዋል።

ሴቶች በሀገር ልማት ያላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያሉባቸውን ጋሪጣ በማስወገድ በህብረተሰቡ የአስተሳሰብ ለውጥ በማምጣት ረገድ ጠንክረው መስራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ክብርት አፈ ጉባኤ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሁክሚያ መሀመድ በበኩላቸው እንደተናገሩት ሴቶች በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፍ እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንዲሁም መብትና ደህንነታቸውን ለማስከበር፣ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል እረገድ በአስተዳደሩ በርካታ የንቅናቄና ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መከናወኑን አንስተዋል።

ሴቶች በሰላም እና በዲሞክራሲ ግንባታ ላይ ያላቸው አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ከአስተዳደሩ ሴቶች ጋር ሰፊ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት በአስተዳደሩ ሰላም እንዲሰፍን ትልቅ ስራ ተሰርተዋል ብለዋል።

በመድረኩ ቀኑን አስመልክቶ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ በተሳታፊዋች ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ከተለያየ ሁለተኛ ደረጃ ተምህርት ቤት ለመጨረሻ ዙር የደረሱ የተማሪዋች ጥያቄና መልስ ውድድር እና በማህፀን ጫፍ ካንሰር መከላከልና ህክምና ዙሪያ በጤና ባለሙያ ገለፃ ተደርጓል። ለውድድሩ አሸናፊዋች እና ለአጋር አካላቶች የእውቅና መረሀ ግብር ተከናውኗል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *