በክብር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ስም በተሰየመው የገንደ ገበታ አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን በማስገንባት ላይ ያለው የኤንዲ ኢንቨስትመንት ግሩፕ(ND Investment Group) ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ የሆነ ኢንጂነር ነገራ ድጉማ ከሀጂ መሀመድ ኡመር ጋር በጋራ በመሆን መጪውን የረመዳን ፆምን በማስመልከት አንድ መቶ ለሚሆኑ አነስተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ፍጆታዎችን በዛሬው እለት ድጋፍ ማድረግ ችለዋል ።
በዚሁ የድጋፍ ስነ-ስርአት ላይም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር እንዲሁም በብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ኢብራሂም ዩሱፍን ጨምሮ ኢንጂነር ነገራ ዱጉማ እና ሀጂ መሀመድ ኡመር በመገኘት ድጋፍን ያበረከቱ ሲሆን ድጋፍ የተደረገላቸው አካትም ምስጋናቸውን በእለቱ አቅርበዋል ።


