በ ኢ. ፌ. ዴ. ሪ የ ህዝብ ተወካዮቸች ምክር ቤት የ ድሬ ዳዋ አስተደዳር ተመራጮች የተከበሩ ዶ/ር ቢፍቱ መሀመድ እና የተከበሩ አቶ አብ ዱልጀዋድ መሀመድ ከህዝቡ ጋር የመራጭ ተመራጮች ውይይት አድርገዋል።
በ ውይይቱ ላይ ከ አራቱም የገጠር ክላስተሮች የ ተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች እና የከተማ አስተዳደር የወረዳ አመራሮች ተሳፈዋል ።
ይህ የ ዉይይት መድረክ ቀደም ሲል በ2015 ዓ.ም የክረምት ወራት በተዘጋጀዉ የ ዉይይት መድረክ ላይ ከሕዝቡ ለተነሱ ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾች እና አሁን በሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ላይ ለመወያየት የ ተዘጋጀ መድረክ መሆኑን በ ኢ. ፌ. ዴ. ሪ. ህ. ተ. ም/ቤት የ ድሬ ዳዋ ተወካይ የ ሆኑ ተመራጮች በመክፈቻ ንግግራቸዉ ገልጸዋል::
ቀደም ሲል በተዘጋጀዉ የ ህዝብ ዉይይት መድረኮች ላይ በተካሄደዉ የ ዉይይት መድረኮች ላይ ከተነሱ የመ ልካም አስተዳደር እና የ ልማት ጥያቄዎች መካከል የመንገድ፣ የውሃ፣ የመብራትና የኔትዎርክ ችግርና የ ዋጋ ንረት ያሰከተለዉ የ ኑሮ ዉድነትና መሰል ጉዳዮች ከሕዝቡ ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል የ ሚጠቀሱ ሲሆኑ
ህዝቡ ያነሱዋቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችና የልማት ጥያቄዎች ምላሽ እንድያገኙ ለማድረግ
በ ፌዴራል መንግስትና በ አስተዳደር ደረጃ ላሉ ጉዳዩ ለሚመለከታቸዉ አካላት በመስጠት ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ መቆየቱንና ከተነሱ የህዝብ ጥያቄዎች መካከል ምላሽ ያገኙ እንዳሉና ግዜ የሚፈልጉ በህደት ላይ ያሉ ያልተመለሱ ጥያቄዎች መኖራቸዉንም ለተሳታፊዎች ማብራሪያ ተሰጥተዋል ።
በመጨረሻም የተከበሩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት የማጠቃላያ አስተያየት የተነሱ ጥያቄዎች በየደረጃው ባለው የ አስተዳደሩ አስፈጻሚ አካል በትኩረት ተይዘው በቅደም ተከተል ሚላሽ እንድያገኙ ጥረት እንደሚደረግ የተከበሩ ዶ/ር ቢፍቱ መሀመድ በማረጋገጥ የዕለቱ የዉይይት መድረኩ ተጠናቁዋል ፡፡


