በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬዳዋ የህዝብ ተመራጭ አባላቶች ከተለያዩ ወረዳዎች ከተወከሉ ህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬዳዋ አስተዳደር የህዝብ ተመራጭ አባል የሆኑት ዶክተር ቢፍቱ መሀመድና አቶ አብዱልጁሀድ መሀመድ ከተለያዩ ወረዳዎች ከተወከሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በአስተዳደሩና በፌደራል ደረጃ ሊፈቱ የሚገቡ የህዝቡ የልማት፣ የኑሮ ማሻሻያ እና አንገብጋቢ የሆኑ መሠረታዊ ጥያቄዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬዳዋ የህዝብ እንደራሴዎች እንደገለፁት መድረኩ ከህዝብ የሚነሱ አንገብጋቢና መሠረታዊ የሆኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ መፍታትን አላማ ያደረገ ነው ፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የተሳተፉ የአስተዳደረ ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም ከመረጧቸው ተወካዮች ጋር ባደረጉት ህዝባዊ ውይይቶች መነሻነት በአስተዳደሩና በፌደራል ደረጃ የሚፈቱ አንገብጋቢ ጥያቄዎች በየደረጃው ምላሽ እያገኙ በመሆናቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬዳዋ አስተዳደር የህዝብ ተመራጭ አባል የሆኑት ዶክተር ቢፍቱ መሀመድና አቶ አብዱጁሀድ መሀመድ በሰጡት ምላሽ ከዚህ ቀደም በተደረጉ ህዝባዊ የውይይት መድረኮች ላይ የተነሱ አንገብጋቢ ጥያቄዎች የመንግስት አቅም በፈቀደው መጠን ምላሽ እንዲያገኙ ሲሰራ እንደነበር ገልፀው በቀጣይም ከህዝብ የተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በትኩረት እንደሚሰራበት አረጋግጠዋል፣ ሌሎች የነዋሪው ጥያቄዎች ላይ የፌዴራል ሚኒስትር መ/ቤቶች ምላሽና እቅዶችን ለገጠሩ ማህበረሰብ በማቅረብ ውክልና የመወጣት ተግባራቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል፡፡


