ቃልን በተግባር ለኢትዮጲያ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል በብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የግማሽ ምርጫ ዘመን አፈፃፀም ለመገምገም እና ለቀሪ የምርጫ ዘመን ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ይቻል ዘንድ የማጠቃለያ ኮንፍረንስ በዛሬው እለት ተካሂዷል ።
በዚሁ መርሀ-ግብር ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር የለውጥ አመራሩ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ከምዕላተ-ህዝቡ ጋር በጋራ በመለየት በአመራሩና በአባላት እንዲሁም በህዝቡ መካከል ያለውን ርቀት ለማጥበብ በሰፊ ህዝባዊ ውይይቶች እና አቅም ግንባታ ሥራዎች ከ 370 በላይ በሹመት የሚገኙ አመራሮች ፣ ከ 50 ሺህ በላይ አባላት እና ከ 250 ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለተውጣጡ የፓርቲያችንን ዕሳቤ በማስረፅ የአመለካከትና የተግባር አንድነት በመፍጠር ነዋሪው ለረጅም ዓመታት ሲያነሳቸው የነበሩ የማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና መልካም አስተዳደር ቁልፍ ጥያቄዎችን ለመመለስ እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ ለነዋሪው ቃል የገባውን የልማት ተግባራት ለማስፈጸም የሚያስችል አሳታፊ የ 10 ዓመት ዕቅድ በማዘጋጀት ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል በተደረገው የተቀናጀ ርብርብ ነዋሪውን ያረኩ እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር የሀገራችን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የሚያስችሉ ጅምር ስኬቶችን እያስመዘገበ እንደሚገኝም ነው ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር በኮንፍረንሱ ላይ የተናገሩት ፡፡
የብልፅግና ፓርቲ የውስጠ ፓርቲ ዲሞክራሲን በድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ግምገማ ፣ ጥናትና ምርምር እንዲሁም ጠንካራ ቅሬታ አፈታት ሥርዓት በመዘርጋት በየወቅቱ ራሱን እያጠናከረ የመጓዝ ልምድ እና አቅም ከመፍጠሩም በተጨማሪ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በትብብር በመስራት ውጤታማ መሆን መቻሉን በመክፈቻው የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ተናግረዋል ።
በኮንፍረንሱ ላይም ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ የወጣ ሲሆን በዚሁ መርሀ-ግብር ላይም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ፣ በብልፅግናንፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ\ሮ ፈቲህያ አደን ፣ የካቢኔ አባላት ፣ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ከፍተኛ አመራሮች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ አባገዳዎች ፣ ኡጋዞች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የብልፅግና ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የወጣቶች ምክር ቤት አመራሮች ፣ የብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች እና ሴቶች ሊግ ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል ።


