የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ ከድር ጁሀር በህብር የመኖርን ባህል በአስተዳደግ አውርሳ የሰብእናችን መገለጫ ቅጽል ፍቅር የሆነበትን የድሬዳዋ እሴት አስቀጥለን ለትውልድ ለማሻገር ፤ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የድሬዳዋ ልጆችና ወዳጆች የጀመሩት የበጎ አድራጎት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል አሉ
በድሬዳዋ ከተማ ለሚኖሩ አቅመ ደካማ ሁለት መቶ ሀምሳ አባወራዎችና እማወራዎች ለፆም ወቅት የሚያግዝ የምግብ አስቤዛ ድጋፍ ሼድ ኦፍ አኪራ በሚል የተሰባሰቡ የድሬዳዋ ልጆች አበርክተዋል ፡፡ በክርስትናና በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚጠበቁት የአብይ የረመዳን አጽዋማት የቅበላ ቀናት ላይ ለሁለት መቶ ሃምሳ አቅመ ደካማ አባወራዎችና እማ ወራዎች ፤ለጾም ወቅት የሚያግዝ የምግብ አስቤዛ ሼድ ኦፍ አኪራ…


