“የተቀናጀ ተፋሰስ ለዘላቂ አረንጓዴ ልማት” በሚል መሪ ቃል ለ18ቀናት ያህል የተከናወነው የተፋሰስ ልማት በቢያዋሌ ክላስተር አዋሌ ቀበሌ የማጠቃልያ መርሀ ግብሩ ተካሂዷል።

በቢያአዋሌ ክላስተር አዋሌ ቀበሌ የዘንድሮ የተፋሰስ ልማት ከመቼውም ጊዜ በላይ አመርቂ ውጤት የተመዘገበበት ሲሆን ስምንት አዳዲስ የውሀ ጉድጓዶች በተባበረና በተቀናጀ ሁሉን አቀፍ ማህበረሠባዊ ስራ ለማግኘት ተችሏል።

የቢያአዋሌ ክላስተር አዋሌ ቀበሌ በተፋሰሱ ልማት ንቅናቄ ላስመዘገበው አስደናቂ ውጤትም የቀበሌው ሊቀመንበር አቶ አብዱለዚዝ መሀመድ የዕውቅና ሠርተፊኬትና ዋንጫ ከድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ከሪማ አሊ እጅ ተረክበዋል።

የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ከሪማ አሊ ቢያአወሌ ክላስተር አዋሌ ቀበሌ ተገኝተው የተፋሰሱ ልማት ማጠቃለያ መርሀ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር በተፋሰሱ ስራ የተገኙት ሰምንቱ ጉድጓዶችና ሌሎችም አመርቂ ውጤቶች በህብረተሠቡ የተቀናጀ ተሣትፎ መሆኑን ጠቅሠው ለአካባቢው ማህበረሰብ ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ምክትል አፈ ጉባኤዋ አክለውም በተፋሰሱ ልማት የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል አስተዳደሩ ሁሉን አቀፍ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግም ቃል ገብተዋል።

በቢያዋሌ ክላስተር አዋሌ ቀበሌ የተፋሰሱ ልማት ማጠቃለያ መርሀ ግብር ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ከሪማ አሊን ጨምሮ የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸውና ሌሎች ስራው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚመለከታቸው አመራሮች ተገኝተዋል።

በድሬደዋ አስተዳደር የተከናወኑ የተፋሰስ ልማት ስራዎች በውሀ ሀብት ግኝት በኩል አመርቂ ውጤት የተመዘገበባቸው እንደሆነ ተገለፀ።

በድሬደዋ አስተዳደር 12ኛ ጊዜ “የተቀናጀ ተፋሰስ ለዘላቂ አረንጓዴ ልማት”በሚል መሪ ሃሳብ የተከናወነውን የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት አስመልክቶ የዕውቅናና የመዝጊያ ስነ ስርዓት በቢያዋሌ ክላስተር አዋሌ ቀበሌ ተካሂዷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *